“በደብረ ብርሃን ከተማ ውሃ ተበክሏል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው” የከተማው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

Debre Birhan town water and sewer office response on the allegations of water poisoning in the town

ሚያዝያ 04፣ 2015

ከተማ ውሃ ተበክሏል ተብሎ የተሰራጨው መረጃሀሰትነው በማለት የከተማው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ /ሪት መሰረት መንገሻ እንደገለጹትከትላንት ጀምሮ መርዝ ተጨምሮበት ውሃ ተበክሏል እየተባለ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ተቋማቸው አንዱ ተግባሩ የሚያመርተውን ውሃ ጥራት አረጋግጦ ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት ሃላፊነታቸው  በመሆኑን ባለሙያዎች እሁድ ቅዳሜን እና የበዓላትን ቀናት ጭምር አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙአስረድተዋል፡፡

የውሃ ማጠራቀሚያ ጋኖች ታጥረው የሚጠበቁ ከመሆኑም በላይ ሁል ጊዜ በባለሙያ ክትትል እየተደረገላቸውውሃው በባለሙያ ጥራቱ ተረጋግጦ ለደንበኞች እንደሚሰራጭ አረጋግጠዋል፡፡

የፀጥታ ችግር ሲከሰት ደግሞ በልዩ ሁኔታ ጥበቃና ክትትል እንደሚደረግላቸው  ጠቁመዋል፡፡ ችግር ካጋጠመምውሃው እንደማይለቀቅ ጠቅሰው ህብረተሰቡ የውሃ ተቋሙ የሚያደርገውን ጥንቃቄ በአግባቡ ተረድቶበአሉባልታ ወሬ እንዳይረበሽ መክረዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::