ስለ ኢትዮጵያ ቼክ

ኢትዮጵያ ቼክ ሰኔ 2020 ዓ.ም የተቋቋመ የመረጃ አጣሪ ተቋም ነው። እአአ ከነሀሴ 2020 ዓ.ም ጀመሮ የኢንተርኒውስ የኢትዮጵያ ፕሮጀክት አካል በመሆን ቆይቷል። በአሁኑ ጊዜ በኬኒያ የተመዘገበ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ነጻ የሆነ የባለአደራ ማህበር በመሆን በመስራት ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያ ቼክ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ሥራዎቹን ለተከታታዮቹ እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ አማካኝነት ከ7 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን መድረስ ችሏል። ኢትዮጵያ ቼክ በአሁኑ ጊዜ የአፍሪካ ፋክትስ ኔትዎርክ አባል ሲሆን የኢንተርናሽናል ፋክትቼኪንግ ኔትዎርክ ፈራሚ ለመሆን አመልክቷል።

ኢትዮጵያ ቼክ በአሁኑ ጊዜ በ3 ዋና ዋና ተግባራት ላይ አትኩሮ ይሰራል። እነሱም: 

  • መረጃ ማጣራት
  • የሚዲያ አጠቃቀም ንቃት ትምህርት መስጠት እና 
  • ስልጠናና የአቅም ግንባታ ስራዎች ናቸው።

ኢትዮጵያ ቼክ ሰኔ 2020 ዓ.ም የተቋቋመ የመረጃ አጣሪ ተቋም ነው። እአአ ከነሀሴ 2020 ዓ.ም ጀመሮ የኢንተርኒውስ የኢትዮጵያ ፕሮጀክት አካል በመሆን ቆይቷል። በአሁኑ ጊዜ በኬኒያ የተመዘገበ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ነጻ የሆነ የባለአደራ ማህበር በመሆን በመስራት ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያ ቼክ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ሥራዎቹን ለተከታታዮቹ እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ አማካኝነት ከ7 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን መድረስ ችሏል። ኢትዮጵያ ቼክ በአሁኑ ጊዜ የአፍሪካ ፋክትስ ኔትዎርክ አባል ሲሆን የኢንተርናሽናል ፋክትቼኪንግ ኔትዎርክ ፈራሚ ለመሆን አመልክቷል።

ኢትዮጵያ ቼክ በአሁኑ ጊዜ በ3 ዋና ዋና ተግባራት ላይ አትኩሮ ይሰራል። እነሱም: 

  • መረጃ ማጣራት
  • የሚዲያ አጠቃቀም ንቃት ትምህርት መስጠት እና 
  • ስልጠናና የአቅም ግንባታ ስራዎች ናቸው።

የኢትዮጵያ ቼክ ባለሙያዎች እነማን ናቸው?

ኤልያስ መሠረት

መስራች/ዋና አርታዒ 

ኤልያስ መሠረት የኢትዮጵያ ቼክ መስራች ሲሆን ከሶስቱ የተቋሙ ባለአደራዎች መካከል አንዱ ነው። በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ቼክ ምስረታ ጀመሮ የመረጃ አጣሪ ተቋሙ ዋና አርታዒ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል። ኤልያስ በጋዜጠኝነት እና በመረጃ አጣሪነት ሰፊ ልምድ ያለው ሲሆን ከ2013 ዓ.ም ጀመሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ውስጥ ሰርቷል። በጋዜጠኝነት እና በመረጃ አጣሪነት ስራውም የ2019 ዓ.ም የጣና ሽልማት አሸናፊ ለመሆን በቅቷል።  በሀሠተኛ መረጃ ስርጭት ዙሪያ በሚያጠነጥነው እና በኢትዮ ኤፍኤም ሬዲዮ ይሰራጭ በነበረው “የልዩ መረጃ” ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ በመሆንም ከ2020 አጋማሽ እስከ 2021 ዓ.ም መጨረሻ አገልግሏል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ማህበርን ከ2020 እስከ 2021 ዓ.ም በፕሬዝደንትነት መርቷል።  

ጽዮን ሞላ

ፕሮግራም ማናጀር

ጽዮን ሞላ ኢትዮጵያ ቼክን በታህሳስ 2022 ዓ.ም በፕሮግራም ማናጀርነት የተቀላቀለች ሲሆን በፕሮጀክት ቀረጽ፣ ክትትል እንዲሁም በለጋሾች ግንኙነት ዙሪያ ተቋሙን በማገልገል ላይ ትገኛለች። ጽዮን ባለፉት ጥቂት ዓመታት የሚዲያ ልማት ፕሮጀክቶችን በመምራት ጥሩ ልምድ አላት።

አሌክሳንደር ዮሃንስ

ፕሮግራም ኮርዲኔተር

አሌክሳንደር ዮሃንስ የሰብአዊ መብት እና የሚዲያ ልማት ፕሮጀክቶችን በመምራት የዓመታት ልምድ አለው። አሌክሳንደር በኢትዮጵያ ቼክ የፕሮጀክት አስተባባሪ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኝ ሲሆን በፕሮግራም ማኔጀር ስር በመሆን ፕሮጀክቶቹ ያለችግር እንዲሄዱ የማስተባበር ስራ ይሰራል። ይህም የግዜ ገደቦችን እና የስራ ሂደትን መቆጣጠር፣ ዝግጅቶችን ማስተባበርን፣ ስብሰባዎችን እና ቀጠሮዎችን ማደራጀትን ያካትታል።  

አዲሱ ፍሬው

መረጃ አጣሪ

አዲሱ ፍሬው ኢትዮጵያ ቼክን በነሀሴ 2020 ዓ.ም የተቀላቀለ ሲሆን በተቋሙ የመረጃ አጣሪ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል። አዲሱ የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያ ሲሆን ጋዜጠኝነትን በመተግበርና በማስተማር የአመታት ልምድ አለው።

ሀብታሙ ጥበቡ

መረጃ አጣሪ

ሀብታሙ ጥበቡ በጋዜጠኝነት እና በመረጃ አጣሪነት የአመታት ልምድ ያለው ባለሙያ ሲሆን ከ2021 ዓ.ም ጀመሮ በኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ አጣሪ በመሆን በማገልገል ላይ ይየገኛል። ሀብታሙ በሬዲዮና በኦላይን ጋዜጠኝነት በርካታ ይዘቶችን የሰራ ባለሙያ ሲሆን በተጨማሪም የመረጃ ማጣራት ስልጠናዎችን የመስጠት ልምድ አለው።

የኢትዮጵያ ቼክ ህጋዊነት

ኢትዮጵያ ቼክ በህጋዊ መንገድ የተመዘገበ ለትርፍ ያልተቋቋመ የመረጃ አጣሪ ተቋም ነው። ተቋሙም በኬንያ ሪፐብሊክ የሰነዶች መዝገብ ቤት በባለአደራ ማህበርነት በፋይል ቁጥር 2252/D7/3174/MMXXII ተመዝግቧል።

የገለልተኝነት መርሆች

ኢትዮጵያ ቼክ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ የሚሰራ የመረጃ አጣሪ ተቋም ነው። ይህን እውን ለማድረግም ባለሙያዎች ተቋሙን ሲቀላቀሉ መርሆቹን የተመለከተ ስልጠና ይሰጣል። የሚከተሉትም ገዥ የገለልተኝነት መርሆቹ ናቸው:

  • የተቋሙ ሰራተኞች ማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ መደገፍ እና/ወይም ዘመቻ ማድረግ አይችሉም
  • የተቋሙ ሰራተኞች የተቋሙን ንብረቶች በመጠቀም ማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ቡድን መደግፍ አይችሉም
  •  የተወሰነ የፖለቲካ አካልን ወይም ግለሰብን የሚጠቅም የመረጃ ማጣራት ስራ ለማድረግ ሲባል የእጅ መንሻ በመቀበል ፈጽሞ የተከለከለ ነው 
  • የተቋሙ ሰራተኞች የተወሰነ የፖለቲካ ፓርቲን ወይም ቡድንን ለመደገፍ በፖለቲካ ስብሰባዎች ወይም ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም
  • የግል ምልከታን ወይም አድሎን በመረጃ ማጣራት ሂደት ውስጥ መቀላቀል ፈጽሞ የተከለከለ ነው

ማሳሰቢያ: እነዚህ መርሆች ጥሰው በሚገኙ ሰራተኞች ላይ ተገቢው ማጣራት የሚደረግ ሲሆን ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።

ድጋፍን በተመለከተ

ኢትዮጵያ ቼክ በኬንያ የተመዘገበ የባለአደራ ማህበር ሲሆን ነሀሴ 2020 እስከ ህዳር 2022 ዓ.ም የኢንተርኒውስ የኢትዮጵያ ፕሮጄክቶች አካልሆኖ ቆይቷል። ከታህሳስ 2022 ዓ.ም ጀመሮ እራሱን የቻለ ነጻ ተቋም በመሆን በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ከታህሳስ 2022 ዓ.ም ጀመሮ ከኢንተርኒውስ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ስራዎቹን በመከውን ላይ የሚገኝ ሲሆን ድጋፉ እስከ ነሀሴ 2023 ዓ.ም የሚቆይ ነው።

ሊጣሩ የሚችሉ መረጃዎችን እንዴት እንመርጣለን?

ኢዮጵያ ቼክ ሊጣሩ የሚችሉ መረጃዎችን የስርጭት መጠናቸውን፣ የሚያደርሱትን ተጽኖ እንዲሁም አንገብጋቢነታቸውን መሠረት በማድረግ ይመርጣል። እንዲሁም ተከታታይነት ያለው የሚዲያ ክትትል በመከውን ሁሉም ድምጾች የሚካተቱበትን አሰራር ይተገብራር።

የእርማትና የቅሬታ ፖሊሲ

ኢትዮጵያ ቼክ እርማቶችን፣ ቅሬታዎችንና ግብረመልሶችን የሚያስተናግድበት ግለጽ አሰራር ያለው ሲሆን  ስህተቶች ከተፈጠሩ ወቅቱን የጠበቀ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል። ለዚህም “እርማት” በሚል ርዕስ ስህተቶችን የሚያርምና የሚያስተካክል ይዘት ያወጣል። በተጨማሪም ባጋራቸው ይዘቶች ላይ ዝማኔ የሚኖር ከሆነ “አፕዴት” በሚል ርዕስ ስር ጭማሬ ያደረጋል። በመረጃ ማጣራ ስራችን ስህተቶችን ከተመለከቱ በሚከተሉት አድራሻዎቻችን ያሳውቁን:

 ኢሜል: [email protected]

 አጭር መልዕክት: +252974058699

እንዲጣራ የሚፈልጉት መረጃ ወይም ጥቆማ አለዎት? መልእክትዎን ይላኩልን::