ይህ ቪዲዮ የአዲስ አበባን ወቅታዊ ሁኔታ አያሳይም

ይህ ቪዲዮ የአዲስ አበባን ወቅታዊ ሁኔታ አያሳይም

መጋቢት 29፣ 2016

ከ37 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘Amhara Youth Association’ የሚል ስያሜ ያለው የትዊተር አካውንት በአዲስ አበባ የተደረገን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ያሳያል ያለው ቪዲዮ ማጋራቱን ተመልክተናል።

ከላይ የተጠቀሰው አካውንት ያጋራው ቪድዮዎም በመቶዎች የሚቆጠር ግብረመልስ ማግኘቱን አስተውለናል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት የተጋራው ቪድዮ ከአውድ ውጭ የቀረበና የቆየ መሆኑን አረጋግጧል። ቪድዮው ከአምስት አመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ተከስቶ የነበረን ግጭትና አለመረጋጋት የሚያሳይ ሲሆን በወቅቱ በርከት ባሉ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ተጋርቶ ነበር።

ከነዚህም አንዱን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል መመልከት ይቻላል: https://youtu.be/2hNFWUmTTyw?si=-xiDFNtAnM-DZuBw

ጊዜያቸውን ባልጠበቀና ከአውድ ውጭ በሆነ መልኩ የሚጋሩ ቪዲዮዎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ጥንቃቄና ማጣራት እናድርግ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::