በላይቤሪያ እያደገ የመጣው የጥላቻ ማዕበል እንዳሳሰባቸው በሀገሪቱ የሚገኙ የሲቪክ ማህበራት ገልጸዋል

UNESCO urges tougher regulation of social media

ግንቦት 25፣ 2015 ዓ.ም

  1. ቻይና ባለፉት ሶስት ወራቶች 1.4 ሚሊዮን በማህበራዊ ሚዲያ የተጋሩ ልጥፎችን (posts) እንዲነሱ እና 67 ሺህ አካውንቶች እንዲሰረዙ ማድረጓል ሮይተርስ ዘግቧል። እርምጃውን የወሰደው የቻይና የሳይበርስፔስ አስተዳደር (Cyberspace Administration of China) መሆኑ የተገለጸ ሲሆን እንዲነሱና እንዲሰረዙ የተደረጉት ልጥፎችና አካውንቶች ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን በማሰረጨት፣ የመንግስት ሹመኞችንና የሌሎች ሰዎችን ስምና ምስል በመጠቀም ሀሠተኛ አካውንት በመክፈት እንዲሁም ሌሎች አሉታዊ ድርጊቶችን በመከውን ተወንጅለው መሆኑ በዘገባው ተካቷል። የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾች ግን እርምጃው ፖለቲካው ይዘት ያለውን ሲሉ መተቸታቸውም ተዘግቧል።
  1. የኔዘርላንድ ፓርላማ ትዊተር በፕላትፎርሙ የሚጋሩ የዛቻና የማስፈራሪያ ይዘቶችን እንዲቆጣጠር ጠይቋል። የፓርላማው አፈጉባዔ ቬራ ቤርካምፕ በጻፉው ግለጽ ደብዳቤ የኔዘርላንድ የህግ አውጭ አባላት በትዊተር አማካኝነት ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች እየደረሰባቸው ቢሆንም ኩባንያው ምንም አይነት እርምጃ እየወሰደ አይደለም ሲሉ ተችተዋል። በትዊተር የሚደርስባቸውን ማስፈራሪያና ዛቻ ተከትሎ የሀገሪቱ የፋይናንስ ሚንስትር ሲግሪድ ካግ እራሳቸውን ከፖለቲካ ለማግለል ማሰባቸውን ከሳምንት በፊት ገልጸው ነበር።
  1. በላይቤሪያ እያደገ የመጣው የጥላቻ ማዕበል በጣም እንዳሳሰባቸው በሀገሪቱ የሚገኙ የሲቪክ ማህበራት በመግለጽ ላይ ናቸው። ኔይሞት ፓርትነርስ ፎር ዴሞክራቲክ ዲቨሎፕመንት የተሰኘ  ድርጅት በዚህ ሳምንት በሰጠው መግለጫ  እያደገ የመጣው የጥላቻ ማዕበል በመጭው ጥቅምት ወር በሀገሪቱ ለሚደረገው ምርጫ ስጋት መፍጠሩን ገልጿል። ድርጅቱ በምግለጫ በተለይም የሀገሪቱ መንግስትና ተቃዋሚ  ፓርቲዎች ጥላቻን የሚያባብሱ መግለጫዎችን ከማውጣት እንዲቆጠቡ ተማጽኗል።

️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን ወቅታዊ መረጃ ለሚዲያ ተቋማት መስጠት ሀሰተኛ መረጃ ለመዋጋት ያለውን አስተዋጵዖ ዳሰናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2018

-እንዲሁም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በተገናኘ የተሰራጨን የማጭበርበር ድርጊት የተመለከተ መረጃ አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2019

-የትግራይ ቴሌቪዥን ስምና አርማን በመጠቀም የተከፈተ ሀሠተኛ የቴሌግራም አካውንትን አጋልጠናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2020

-ስለሀሰተኛ መረጃ ግንዛቤ የሚሰጥ ጽሁፍ በአፋን ኦሮሞ አስነብበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2021

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::