ዩቱብ ፖሊሲዎቹን ለሚጥሱ ይዘት ፈጣሪዎች ስልጠና መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ነሐሴ 26፣ 2015 ዓ.ም

  1.  ዩቱብ ፖሊሲዎቹንና መርሆዎቹን ለሚጥሱ ይዘት ፈጣሪዎች ስልጠና መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል። ስልጠናውን የሚወስዱት ይዘት ፈጣሪዎች የፖሊሲና የመርህ ጥሰት የፈጸሙና ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑ ተገልጿል። ስልጠናው ለምን ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ግንዛቤ የሚያስጨብጥ እንደሚሆንም ተነግሯል። በዚህም የይዘት ፈጣሪዎችን ስነምግባር ለማጎልበትና የሚዘጉ ቻናሎችን ለመቀነስ መታሰቡ ተገልጿል።
  1.  ጎግል በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ የተፈበረኩ ምስሎችን ለመለየት የሚያስችል መገልገያን (tool) ወደስራ ለማስገባት ሙከራ መጀመሩን በቴክኖሎጅ ጉዳይች ላይ የሚዘግበው ዘ ቨርጅ አስነብቧል። ይህ ሲንትአይዲ (SynthID) የሚል መጠሪያ የተሰጠው መገልገያ በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ የተፈበረኩ ምስሎችን በቀልሉ መለየት እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል። መገልገያው ኢሜጅን (Imagen) በተሰኘው የጎግል የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ የተመረቱ ምስሎችን በመለየት ስራ እንደሚጀምርም ተነግሯል።
  1. ቲክቶክ በተቀናጀ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት እና ተጽኖ ፈጠራ ላይ ተሰማርተው ነበር ያላቸውን 284 አካውንቶች ማገዱን አለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል። አካውንቶቹ መሰረታቸውን ቻይና ያደረጉ መሆናቸውም ተጠቅሷል። ቲክቶክ በቻይና አካውንቶች ላይ የወሰደው እርምጃ ያልተለመደ መሆኑም ተዘግቧል።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው፥

– በሰኞ መልዕክታችን በማህበራዊ ሚዲያ ስለሚጋሩ አደገኛ ይዘቶች ምንነት የሚያስረዳ ጽሁፍ አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2156

– በደበረታቦር ከተማ የተከሰተ ግጭትን ያሳያሉ ተብለው የተጋሩ ምስሎችን ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2157

– በተመሳሳይ በደብረ ማርቆስ ከተማ የተማረኩ ሄሊኮፕተሮችን ያሳያሉ ተብለው የተጋሩ ምስሎችንም ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2158

– በኢትዮጵያ ለሽያጭ የቀረቡ ሴቶችን ያሳያል ተብሎ የተጋራ ምስል ላይም ማጣራት አድርገናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2161

https://t.me/ethiopiacheck/2162

https://t.me/ethiopiacheck/2163

– አቶ በቀለ ገርባን በተመለከተ ኦፌኮ አወጣው ተብሎ የተሰራጨን ደብዳቤም ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2165

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::