ትዊተር የጥላቻ ይዘት ያላቸውን ትዊቶች ተደራሽነት በ81% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን አስታወቀ

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ሐምሌ 07፣ 2015

  1. አውሮፓ ህብረት በአባል ሀገራቱ አመጽ፣ አለመረጋጋትና ግጭት በሚኖርበት ወቅት የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎትን ለመዝጋት የሚያስችል ህግ ወደ ስራ ሊያስገባ መሆኑን ፖለቲኮ ዘግቧል። በመጭው ነሀሴ ወር መጨረሻ ወደ ትግበራ የሚገባው አዲሱ ህግ ግድያን፣ መኪና ማቃጠልን ወዘተ የመሳሰሉ ጥላቻ አዘል ይዘቶች የማይቆጣጠሩ የማህበራዊ ሚዲያ ተቋማት ላይ የመዝጋት እርምጃ ይወስዳል ተብሏል። ህጉ ትዊተርንና ቲክቶክን ጨምሮ 15 የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ኩባንያዎች ን ይቆጣጠራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ፖለቲኮ በዘገባው አካቷል።
  1. ትዊተር የጥላቻ ይዘት ያላቸውን ትዊቶች ተደራሽነት (reach) በ81% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን አስታወቀ። 700,000 ትዊቶች ግርጌም የጥላቻ ይዘት ያላቸው መሆኑን የሚገልጽ መረጃ (labels) እንዲነበብ ማድረጉን ገልጿል። ኩባንያው የጥላቻ ይዘት ያላቸውን ትዊቶች ከማገድ ይልቅ ተደራሽነታቸውን መቀነስ አላማው መሆኑን ከወራት በፊት አስታውቆ ነበር። በዚህ ‘Freedom of Speech Not Reach’ የሚል ስያሜ በተሰጠው አሰራር ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ሳይጎዱ አሉታዊ ይዘቶችን መቀነስ ይቻላል የሚል እምነቱን ገልጾ ነበር።
  1. “ጥራት ያለው መረጃ ለተሻለ ነገ” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሚዲያ ልማት ጉባዔ በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ ተካሄደ። በጉባዔው ከ45 አገሮች የተወጣጡ 300 የመረጃ አጣሪዎች እና የምርመራ ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ ቼክም በጉባዔው ተገኝቷል። በጉባዔው ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች እያደርሱ ያሉትን ጉዳትና መፍትሄዎችን እንዲሁም የሰው-ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ (AI) ከመረጃ ፍሰት አንጻር የደቀነውን ስጋት እና ተስፋ የተመለከቱ ውይይቶች ተደርገዋል። ከሀምሌ 5 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ ለሶስት ቀናት የተካሄደውን ጉባዔ ያሰናዳው ሲኤፍአይ ሚዲያ ዲቨሎፕመንት (CFI Media Development) ከአፍሪካ ቼክ (Africa Check)፣ ከአረብ ሪፖርተርስ ፎር ኢንቨስቲጌቲቭ ጆርናሊዝም (ARIJ) እና ከአፍሪክቲቪስትስ (AfricTivistes) ጋር በመተባበር ነበር።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን በፈጣን መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎች ስለሚጋሩ አሉታዊ ይዘቶች የሚያትት ጽሁፍ አስነብበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2075

-ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአማርኛና የታሪክ ትምህርት ክፍሎችን ሊዘጋ ነው ስለመባሉ ያሰባሰብነውን መረጃም አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2076

-የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለሚገኝ የስራ አጦች ቁጥር መጨመር ለጨፌ ያቀረቡትን የተሳሳተ መረጃ ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2079

https://t.me/ethiopiacheck/2078

-የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት በሆነው M-PESA ስም እየተሰራጩ የሚገኙ የማጭበርበሪያ መረጃዎችን የተመለከተ ጽሁፍም አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2080

-ሀሰተኛ መረጃን ለመለየት ስለሚያግዝ መገልገያም ጽሁፍ አጋርተናል: https://t.me/ethiopiacheck/2082

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::