ቲክቶክን በመጠቀም በቀልድ ተለውሰው የሚቀርቡ የጥላቻ ንግግሮች ለመቀነስ ማድረግ የምንችለው አስተዋጾ

twitter verification

ሚያዝያ 09፣ 2015

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ከብሔር፣ ከሀይማኖትን እንዲሁም ከሌሎች ሌሎች ማንነቶች አንጻር የሚሰነዘሩ የጥላቻ መልዕክቶች ከሚተላለፉባቸው ዘዴዎች መካከል ቀልዶች ይጠቀሳሉ። እነዚህ ቀልዶች በጽሁፍ፣ በንግግር፣ በምስል፣ በቪድዮ ቅርጽ ሊቀርቡ ይችላሉ።

በቀልድ መልክ የሚተላለፉ የጥላቻ መልዕክቶች በርከት ያለ አድማጭ፣ አንባቢና ተመልካች የመሳብ አቅማቸው እንዲሁም ዳግም የመጋራት ዕድላቸው ከፍ ያለ መሆኑ የሚያደርሱት ጉዳትም በዛም መጠን እንደሚጨምረው ይታመናል።

እንዲህ ያሉ በማር የተለወሱ የጥላቻ መልዕክቶች ከሚጋሩባቸው የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቲክቶክ በቀዳሚነት እንደሚጠቀስ ብዙዎቹ ይስማማሉ። በሀገራችንም ይህ በስፋት እንደሚስተዋል ተመልክተናል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት በርከት ያሉ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ወጣቶችና ታደጊዎች ሲሆኑ ይህም የሚተላለፉ የጥላቻ መልዕክቶች መሬት ላይ ወርደው ሊደርሱ የሚችሉትን ጥፋት አሳሳቢ ያደርገዋል።

ቲክቶክን በመጠቀም በቀልድ ተለውሰው የሚጋሩ የጥላቻ  መልዕክቶች በማህበረሰቦች መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ እንዳያሻክሩት ብሎም ግጭት እንዳያቀጣጥሉ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይጠበቅብናል።

በይዘቶቹ አለመሳተፍ፣ ይዘቶቹን አለማጋራት እንዲሁም እንዲህ ያሉ ይዘቶችን የሚያጋሩ አካውንቶችን አለመከተል አንድ አበርክቶት ሊሆን ይችላል።

ሪፖርት ማድረግ ደግሞ ሌላው ልናበረክተው የምንችል በጎ አስተዋጾ ነው።  ሪፖርት ለማድረግም ቲክቶክ ቀለል እና በርከት ያሉ አማራጮች አሉት:

1. ቪዲዮ ሪፖርት ለማድረግ:-

•ሪፖርት ለማድረግ ወደፈለጉት ቪዲዮ ይሂዱ፤

•ቪዲዮውን ተጭነው ትንሽ ይቆዩ፤

•ቀጥሎ “Report” የሚለውን ይጫኑ፤

•ከዚያም “Hateful behavior” የሚለውን ይምረጡ፤

•በመጨረሻም ሪፖርትዎን ያስገቡ።

2. በቀጥታ በመተላለፍ ላይ ያለን ቪዲዮ (Live Video) ሪፖርት ለማድረግ፦

•በቀጥታ በመተላለፍ ላይ ወደሚገኘው ቪዲዮ ይሂዱ፤

•ከዚያም “Share” የሚለውን ይጫናኑ፤

•ቀጥሎ “Report” የሚለውን ይጫኑ፤

•ከዚያም “Hateful behavior” የሚለውን ይምረጡ፤

•በመጨረሻም ሪፖርትዎን ያስገቡ።

3. አስተያየትን (comment) ሪፖርት ለማድረግ፦

•ሪፖርት ማድረግ ወደፈለጉት አስተያየት ይሂዱ፤

•አስተያየቱ ላይ ተጭነው ትንሽ ይቆዩ፤

•ቀጥሎ “Report” የሚለውን ይጫኑ፤

•ከዚያም “Hateful behavior” የሚለውን ይምረጡ፤

•በመጨረሻም ሪፖርትዎን ያስገቡ።

4. አካውንት ሪፖርት ማድረግ ከፈለጉ፦

•ሪፖርት ማድረግ ወደፈለጉት አካውንት ይሂዱ፤

•ከዚያም በስተቀኝ ከላይ የሚታዩትን ሶስት ነጠብጣቦች (…) ይጫኑ፤

•ቀጥሎ “Report” የሚለውን ይጫኑ፤ ከዚያም መመሪያዎችን ይከተሉ።

ሀሰተኛ እና የጥላቻ ንግግሮችን የያዙ ምስሎችን፣ ፅሁፎችን እና ቪድዮዎችን ሪፖርት በማድረግ እና ባለማጋራት ሀላፊነታችንን እንወጣ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::