ቲክቶክ የአርትዖ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑ ተገለጸ

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ነሐሴ 05፣ 2015 ዓ.ም

  1. ቲክቶክ የአርትዖ (editing) አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን በቴክኖሎጅ ጉዳዮች ላይ የሚዘግበው ዘ ሊፕ አስነብቧል። የአርትዖ አገልግሎቱ የቲክቶክ ደንበኞች የግርጌ ጽሁፎችን (captions)፣ ሃሽታጎችን፣ ማብራሪያዎችን እና ሌሎች ጽሁፎችን እንዲያስተካክሉና እንዲያዘምኑ ያስችላል ተብሏል። አገልግሎቱ የሚሰራውም ከተጋሩ ከሰባት ቀን በላይ ላልበለጣቸው ይዘቶች መሆኑን ዘ ሊፕ ዘግቧል።
  1. ፌስቡክ ለረጅምም ጊዜ ንቁ (active) ያልሆኑ የግሩፕ አስተናባሪዎችን (admins) በሌሎች የግሩፑ አባላት እንደሚተካ አስታውቋል። ፌስቡክ እንደሚለው የግሩፕ አስተናባሪዎች በግሩፑ የሚጋሩ ይዘቶችን የመከታተል እና የመቆጣጠር ሃላፊነት ያለባቸው ሲሆን ረዘም ላለ ጊዜ ንቁ ያልሆኑ አስተናባሪዎች በሌላ ሰው እንዲተኩ ማሳሰቢያ መስጠት ጀምሯል። አስተናባሪዎች ራሳቸው ሌላ ሰው መተካት ካልቻሉ ፌስቡክ ሌላ የግሩፑ አባል አስተናባሪዎች እንዲሆን የመጋበዝ ስራ እንደሚሰራ አስታውቋል።
  1. የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅን የሚገዙ ህጎች ሊኖሩ ይገባል ሲሉ በርከት ያሉ አለም አቀፍ የሚድያ ተቋማት እና ማህበሮች በትናንትናው ዕለት ባሰራጩት ግልጽ ደብዳቤ ጠይቀዋል። ኤፒ፣ ኤኤፍፕ፣ ጌቲ ኢሜጅስን ጨምሮ ሌሎች የሚድያ ተቋማት እና ማህበራት በጻፉት ደብዳቤ የየሀገራቱ ህግ አውጭዎች የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅን የሚገዙ ህጎች እንዲያወጡ ጠይቀዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅን በማበልጸግ የተሰማሩ ኩባንያዎችም የዳታ አጠቃቀምን በተመለከተ ከሚዲያ ተቋማት እና ማህበራት ጋር ድርድር እንዲያደርጉ እንዲሁም በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ ይዘቶችን እንዲያሳውቁ፣ ሀሰተኛ መረጃን እና መድሎን እንዲከላከሉ ጠይቀዋል።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ድንበሩ የት ድረስ ነው በሚል ርዕስ በአፋን ኦሮሞ ጽሁፍ አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2119

-ለኢፌዴሪ አየር ሃይል እንደተጻፈ ተደርጎ የተጋራን ደብዳቤ ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2123

-ከሰሞኑ በአማራ ክልል የተማረኩ ወታደሮች ናቸው ተብሎ የተሰራጨን ምስል አጣርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2124

-እንዲሁም ከሰሞኑ በአማራ ክልል የተማረኩ የጦር መሳሪያዎችን ያሳያል ተብሎ የተጋራን ምስል አጣርተን በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2127

https://t.me/ethiopiacheck/2126

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::