በኬንያ ቲክቶክ ላይ የሚወጡ ቪዲዮች ቁጥጥር እንዲደረግባቸው ከኩባንያው ጋር መስማማቷን ሀገሪቱ አስታውቃለች

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ነሐሴ 19፣ 2015 ዓ.ም

  1. በኬንያ ቲክቶክ ላይ የሚወጡ ቪዲዮች ቁጥጥር እንዲደረግባቸው ከኩባንያው ጋር መስማማቷን ቪኦኤ ዘግቧል። ስምምነቱ የተደረሰው “ቲክቶክ ያልተገቡ ቪዲዮዎችን ያሰራጫል” በሚል እንዲታገድ ከአንድ ግለሰብ ለሀገሪቱ ፓርላማ ከቀናት በፊት ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ መሆኑም በዘገባው ተካቷል። በስምምነቱ መሠረት፣ “ያልተገቡ ናቸው” የሚባሉ ቪዲዮች ከመድረኩ እንደሚወገዱ ታውቋል። በአፍሪካ በቲክቶክ ላይ የሚወጡትን የቪዲዮዎች ይዘት በተመለከተ ቁጭር ለማድረግ ኩባንያው በኬንያ ቢሮ እንደሚከፍት ዋና ሥራ አስፈጽሚው ሾ ዚ ችው ይፋ ማድረጋቸውም ተነግሯል።
  1. ሱማሊያ ቲክቶክን እና ቴሌግራምን ማገዷን አልጀዚራ ዘግቧል። ሀገሪቱ ሁለቱን ፕላትፎርሞች ያገደችው የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች እና የአሰቃቂ ይዘቶች መናህሪያ ሆነዋል በማለት መሆኑን አልጀዚራ በዘገባው አካቷል። በሱማሊያ የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጡ ኩባንያዎች ፕላትፎርሞቹን ከትናት ጀምሮ እንዲያግዱ ትዕዛዝ መሰጠቱም ታውቋል።
  1. የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከሁለት አመት በኃላ ወደ ኤክስ (በቀድሞ ስሙ ትዊተር) ተመልሰዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ “የኃይል ድርጊትን ማነሳሳትና ማበረታታት” የሚለውን የትዊተር ፖሊሲ ጥሰዋል ተብሎ ከሁለት አመት በፊት እግድ ተጥሎባቸው እንደነበር ይታወቃል። ባለጸጋው ኤሉን መስክ ፕላትፎርሙን ከገዛው በኃላ የትራምፕ እግድ ስህተት መሆኑንና ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት ጋር እንደሚጣረስ ደጋግሞ ሲገልጽ ይሰማ ነበር።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው፥

  • በሰኞ መልዕክታችን በማህበራዊ ሚዲያ ስለሚሰራጩ አደገኛ መልዕክቶች ግንዛቤ የሚፈጥር ጽሁፍ አስነብበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2146

  • በስንቄ ባንክ ስም ተመሳስለው የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾችን የሚያጋልጥ መረጃ አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2148

  • ኢትዮጵያ የብሪክስ ሀገራት አባል ሆነች ተብሎ የተሰራጨን መረጃ ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2150

  • በቲክቶክ የሚጋሩ ሀሠተኛ እና የተዛቡ ይዘቶችን ለመለየት የሚረዱ ነጥቦችን የሚጠቁም ጽሁፍ አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2151

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::