ይህ ምስል በኢትዮጵያ የተከሰከሰ ድሮንን አያሳይም

ይህ ምስል በኢትዮጵያ የተከሰከሰ ድሮንን አያሳይም

ጥር 16፣ 2016

ከ880 በላይ ተከታዮች ያሉት እና ‘Tordit-ቶ’ የሚል መጠሪያ ያለው የትዊተር አካውንት ንብረትነቱ የኢትዮጵያ የሆነ ድሮን መከስከሱን ያሳያል ያለውን ፎቶ አጋርቷል። አካውንቱ የድሮን መከስከሱን ያሳያል ያለው ፎቶ የት እና መች መወሰዱን አልገለጸም።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት የትዊተር አካውንቱ ያጋራው ፎቶ የቆየና ከሌላ ቦታ የተወሰደ መሆኑን አረጋግጧል።

በፎቶው ላይ የሚታየው ድሮን ንብረትነቱ የእስራኤል ሲሆን እ.አ.አ መጋቢት 31/2018 ዓ.ም በሊባኖስ የተከሰከሰ መሆኑን ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል በወቅቱ የሰራው ዘገባ ያሳያል።

ትክክለኛውን ፎቶም ይህን ማስፈጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል:

https://www.timesofisrael.com/hezbollah-tv-says-israeli-spy-drone-crashed-in-lebanon/

ጊዜያቸውን ባልጠበቀና ከአውድ ውጭ በሆነ መልኩ የሚጋሩ ፎቶዎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ጥንቃቄና ማጣራት እናድርግ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::