ሶሻል ሚድያ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሚና ምን ያህል ነው?

ሶሻል ሚድያ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሚና ምን ያህል ነው?

ሐምሌ 11፣ 2015

ኢትዮጵያ ቼክ በትናንትናው እለት “የሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግሮችን በማስፋፋት ረገድ ሶሻል ሚድያ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሚና ምንድን ነው ብለው ያስባሉ?” የሚል ጥያቄን ለተከታታዮቹ አቅርቦ ነበር።

በተሰጠው ድምፅ መሰረት 51% የተፈጠሩ ችግሮች እንዲባባሱ ሚና ተጫውቷል፣ 40% ችግሮቹ እንዲፈጠሩ ምክንያት ነው፣ 5% ችግሮቹ እንዳይባባሱ አስተዋፅኦ አበርክቷል፣ 2% በችግሮቹ ዙርያ ምንም አስተዋፅኦ አልነበረውም እንዲሁም 2% መልሱ አልተሰጠም ሆኗል።

በአጠቃላይ 486 ሰዎች ድምፅ በመስጠት ተካፍለዋል።

በኢትዮጵያም ሆነ በአለም ዙርያ የማህበራዊ ሚድያዎች ለበርካቶች ዋነኛ የዜና ማግኛ ዘዴ ከሆኑ ሰነባብተዋል። እንደውም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጋዜጣ ከመግዛት ይልቅ በስልካቸው ዜና ማግኘት ይቀላቸዋል፣ ቴሌቭዥን እና ሬድዮ ከመመልከት እና ከመስማት ይልቅ ፌስቡክን ወይም ቴሌግራምን በቀላሉ መጠቀምን ይመርጣሉ።

ይህ ወደ ማህበራዊ ሚድያ በፍጥነት የሚደረገውን ጉዞ ተከትሎ ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ የዜና ተቋማትም ዜናዎቻቸውን እዚያው ላይ ያቀርባሉ፣ ግለሰቦች እና ሌሎች ድርጅቶችም መረጃዎችን እና ሀሳቦችን በስፋት ያንሸራሽራሉ።

የመረጃ ፍሰቱ ወደ ማህበራዊ ሚድያ ድርጅቶች ማጋደሉ በራሱ ችግር ባይሆንም ይህን ተከትሎ አንዳንድ አካላት ሀሰተኛ መረጃዎችን እና የጥላቻ ንግግሮችን በቀላሉ እንዲያስተላልፉ በር ከፍቷል።

ይህም በራሱ ቀውሶችን ፈጥሯል ማለት ባይቻል እንኳ የተከሰቱ ችግሮችን በማባባስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፣ እያደረገም ይገኛል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::