ለአንድ ሀሰተኛ መረጃ በስፋት መሰራጨት ምን ምክንያት ሊሆን ይችላል?

Telegram poll on the causes for the spread of false information

የካቲት 22፣2015

ኢትዮጵያ ቼክ በትናንትናው እለትአንድ ሀሰተኛ መረጃ በስፋት እንዲሰራጭ ምክንያት የቱ ሊሆን ይችላል?” የሚል ጥያቄን ለተከታታዮቹ አቅርቦ ነበር።

ለዚህ ጥያቄ 883 ሰዎች መልስ የሰጡ ሲሆን በዚህም መሰረት ያሰራጨው አካል ታዋቂ ከሆነ (ብዙ ተከታይያለው) ሲሆን 14% የቀረበው መረጃ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን 13% መረጃው የተጋነነ እና ስሜትኮርኳሪ ሲሆን 11% መረጃው በቅንብር ምስል እና ቪድዮ የተደገፈ ሲሆን 5% መረጃው በሚድያ አማካኝነትሲቀርብ 3% እንዲሁም 54% ሁሉም መልስ ነው የሚል መልስ ተሰጥቷል።

ብዙ ሰዎች እንደጠቆሙት ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች በሙሉ ሀሰተኛ መረጃ በስፋት እንዲሰራጭ ምክንያትየመሆን እድላቸው ከፍ ያለ ነው።

በተለይ የፖለቲካ አለመረጋጋት ወይም ግጭት ሲኖር በየሰዐቱ የሚፈጠሩ ክስተቶችን ለማወቅ ጉጉታችንይጨምራል። የማወቅ ጉጉታችንን ለማርካት መረጃ ልናገኝባቸው እንችላለን ያልናቸውን የማህበራዊ ሚዲያገጾች ወይንም ቻናሎች አልያም ሚዲያዎች ማሰሳችን ይጠበቃል። በአሰሳችን ወቅት ለክሊክ አጥማጆች(clickbaits) የመጋለጥ እድልም ይኖረናል።

የክሊክ አጥማጆች ለስሜታችን የቀረበ፣ ጉጉት የሚያጭር፣አትለፉኝ አትለፉኝየሚል የዜና ርዕስ (headline) እናበደንብ የተቀናበረ ፎቶ በመጠቀም ማስፈንጠሪያዎችን እንድንከተል ወይንም ቪዲዮዎችን እንድንከፍትየሚገፋፉ ገጾችና ቻናሎች ሲሆኑ ወደ ውስጥ ገብተን ይዘታቸውን ስንመለከት ከዜና ርዕሳቸው ጋር የማይገናኝ፣ምንጭ የሌለው፣ ከዚህም ከዚያም የተቃረመ ሆኖ እናገኘዋለን።

ክሊክ አጥማጆች በኢትዮዮጵያ በተለይ በዩትዩብ በርከት ብለው የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹ አላማቸው ብዙሰብስክራይበርና ተመልካች በማግኘት ብር ማግኘት ሲሆን ሌሎቹ የፖለቲካ አላማቸውን ለማሳካትይጠቀሙበታል።

ክሊክ አጥማጆች በአብዛኛው ይዘታቸው ምንጭ የማይጠቅስ፣ የተጋነነ፣ ርዕታዊነት የጎደለውና ወገንተኛ ሆኖይገገኛል። በዚህም ለሀሠተኛና የተዛቡ መረጃው ስርጭት ከፍተኛ ድርሻ ይወስዳሉ።

ስለሆነም በክሊክ አጥማጅ የዩቲዩብ ቻናሎች ወይንም ድረገጾች የሚቀርቡ መረጃዎችን ከማመናችን እናከማጋራታችን በፊት ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::