በዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ስም የወጣ ሀሠተኛ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

በዩኒሴፍ ኢትዮጵያ

ሰኔ 24፣ 2015 ዓ.ም

ኒሴፍ ኢትዮጵያ በ6 ክልሎች 2,800 ሰራተኞችን ለመቅጠር  እንደሚፈልግ የሚገልጽ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ በማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት ሲዘዋወር ተመልክተናል። ማስታወቂያው ለመመዝገቢያ ማመልከቻ ፎርም ብር የሚጠይቅ ሲሆን ክፍያውንም በሲቢኢ ብር ወይም በቴሌብር ቀድመው እንዲከፍሉ ያሳስባል።

ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ይህ የስራ ማስታወቂያ ሀሠተኛ መሆኑን አስታውቋል። ድርጅቱ የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን በ UNICEF Careers | UNICEF Careers ድረገጽ ብቻ እንደሚያስተዋውቅም ገልጿል። በተጨማሪም ዩኒሴፍ በየትኛው የቅጥር ሂደት ገንዘብ እንደማያስከፍል የገለጸ ሲሆን የባንክ መረጃም እንደማይጠይቅ አስታውቋል።

በሀሠተኛና ግልጽነት በጎደላቸው ማስታወቂያዎች አማካኝነት ከሚከሰት መጭበርበር እራሳችንን ለመጠበቅ ጥንቃቄ እናድርግ!

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::