በሚድሮክ ኢንቨስትመት ግሩፕ ስም የተከፈተ ሀሠተኛ የቴሌግራም አካውንት ያሰራጨው የማጭበርበር ድርጊት

fake telegram channel impersonating midroc investment group

መጋቢት 11፣ 2016

ከ4,600 በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘MIDROC INVESTMENT GROUP’ የሚል ስያሜ ያለው የቴሌግራም አካውንት “ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ደንበኞቹን የቤት ባለእድለኛ ሊያረግ ነው” የሚሉ ተከታታይ መልዕክቶችን ሲያጋራ ተመልክተናል።

በመልዕክቱም ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2015 መጨረሻ   ለደንበኞቹ “ያጋሩ ይሸለሙ” በሚል መሪ ቃል የ2022 ሞዴል ሱዙኪ ዲዛየር መኪና እንዲሁም ሌሎች ሽልማቶችን መስጠቱን ገልጿል።

አሁን ደግሞ ሁለተኛ ዙር ሽልማት መጀመሩ የተለያዩ ስፋት ያላቸው የመኖሪያ ቤቶችን፣ ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ  ሞተር እና የአመት ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት ለሽልማት ማዘጋጀቱን አስነብቧል። ሽልማቱን ለማግኘትም መልዕክቶቹን በተደጋጋሚ ‘ሼር’ እና ‘ፎርዋርድ’ ማድረግ መስፈርት መሆኑን ይገልጻል።

ኢትዮጵያ ቼክ ከላይ የተጠቀሰውን የቴሌግራም ቻናል ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን አነጋግሯል።  የግሩፑ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳሬክቶሬት ሃላፊ አቶ ሰይድ ሞሐመድ ቻናሉም ሆነ በቻናሉ የተላለፉ መልዕክቶች ትክክለኛ አለመሆናቸውን ነግረውናል።

አቶ ሰኢድ ትክክለኛው የሚድሮክ የፌስቡክገፅ https://www.facebook.com/midroc.username እንዲሁም የቴሌግራም ቻናል https://t.me/midrocinvestmentgroup መሆኑን ከዚህ በፊት አሳውቀው ነበር።

ተመሳስለው በሚከፈቱ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች አማካኝነት በሚሰራጩ የማጭበርበር ድርጊቶች ሰለባ ላለመሆን ጥንቃቄ እናድርግ!

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::