የሶሻል ሚድያ ኩባኒያዎች የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች እንዴት ይመለከቱታል?

Public opinion results about social media companies

ጥቅምት 26፣ 2016 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ቼክ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ “ሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግሮችን ከፕላትፎርማቸው በማስወገድ ረገድ የሶሻል ሚድያ ኩባንያዎች የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች እንዴት ይመለከቱታል?” የሚል ጥያቄን ለቴሌግራም ተከታታዮቹ አቅርቦ ነበር።

በተሰጠው መልስ መሰረትም 49% በቂ ስራ እየሰሩ አይደለም፣ 21% ምንም ስራ እየሰሩ አይደለም፣ 17% በዚህ ዙርያ ስራ ሲሰሩ ተመልክቼ አላውቅም፣ 6% በቂ ስራ እየሰሩ ነው እንዲሁም 7% በዚህ ዙርያ የተለየ ሀሳብ አለኝ ሆኗል።

በአጠቃላይ 432 ሰዎች ድምፅ በመስጠት ተካፍለዋል።

እንደ ፌስቡክ፣ ጉግል፣ ቴሌግራም እና ትዊተርን የመሳሰሉ የማህበራዊ ትስስር መድረኮች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው ይታወቃል።

በኢትዮጵያ ህግም ያስገድዳቸዋል።

እነዚህን መድረኮች ትክክለኛ መረጃ የሚያሰራጩ ገጾችና ቻነሎች በቅድሚያ የመታየት ዕድል እንዲያገኙ በማስቻል፤ ዜጎች ሀሠተኛ መረጃን ሪፖርት የሚያደርጉበትን አካሄድ ቀላል እና በሚረዱት ቋንቋ እንዲሆኑ በማድረግ እንዲሁም ሪፖርቶችን እና ይዘቶችን የሚከታተሉ በቂ ባለሙያዎችን በመመደብ የሀሠተኛ መረጃ ስርጭት እንዲቀንስ ሀላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::