ተቋማት መረጃ በመስጠት የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን የመከላከል ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል

twitter verification

ግንቦት 21፣ 2015 ዓ.ም

ከቅርብ አመታት ወዲህ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት በሰፊው አነጋጋሪ እንዲሁም አሳሳቢ ሆኗል። ጊዜው የጠበቀ፣ የተሟላና ትክክለኛ መረጃ ለዜጎች ማቅረብ ደግሞ የጋዜጠኞች እና የሚዲያ ተቋማት ተቀዳሚ ስራ ነው።

ይህን የየዕለት ተግባራቸውን ለመፈጸም ደግሞ በቅድሚያ ጊዜው የጠበቀ፣ የተሟላና ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል።

ሆኖም መረጃ ማግኘት መሰናክሉ ብዙ ነው። የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ሃላፊዎች በአብዛኛው ለጋዜጠኛና ለሚዲያ ተቋማት በራቸው ዝግ ነው።

የየተቋማቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችም እንዲተላለፍ የሚፈልጉት መረጃ ከመስጠት ባለፈ ከጋዜጠኞችና ከሚዲያ ተቋማት የሚቀርብላቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ ብዙም ፍላጎት አያሳዩም።

መረጃ ላለመስጠት ብዙ ስበብ ማስቀመጥ የተለመደ ነው።

ከጥቂት ተቋማት ድረገጾች ውጭም ጊዜው የጠበቀ፣ የተሟላና ትክክለኛ መረጃ ማግኘትም የማይታሰብ ነው።

እንዲህ ያሉት መረጃን ከማግኘት አንጻር የተቀመጡ ማነቆዎች ዜጎች ጊዜው የጠበቀ፣ የተሟላና ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኙ ያደርጋሉ።

ይልቁንም ሀሠተኛና የተዛባ መረጃ፣ የጥላቻ ንግ ግር እንዲሁም የሴራ ትንተና ቦታውን ይይዛሉ።

ይህ ደግሞ በማህበረሰቦች መካከል ያለ ትስስርን ይሸረሽራል። በዜጎችና በመንግስት መካከል ያለ መተማመን ይቀንሳል። ብሎም ለጥላቻ፣ ለግጭት፣ ለውድመት፣ ለጦርነት፣ ለረሃብ፣ ለስደትና ለሞት ይዳርጋል።

እንዲህ ያለውን ምስቅልቅል ለመከላከል ሀሠተኛ መረጃን በእውነተኛ መረጃ መመከት ግድ ይላል።

ለዚህ ደግሞ ተቋማት ጊዜው የጠበቀ፣ የተሟላና ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::