የትኞቹም የምስል ማሰሻዎች/ማጣርያዎች ተጠቅመው ያውቃሉ?

poll result

ሰኔ 18፣ 2015 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ቼክ በትናንትናው እለት “ከሚከተሉት የምስል ማሰሻዎች/ማጣርያዎች ውስጥ የትኛውን ተጠቅመው ያውቃሉ?” የሚል ጥያቄን ለተከታታዮቹ አቅርቦ ነበር።

በተሰጠው ድምፅ መሰረት 28% Google Images፣ 23% Google Lens፣ 8% Pinterest፣ 6% TinEye፣ 3% Yandex እንዲሁም ከሁሉም የበለጠ ቁጥር ያላቸው ወይም 58% የሚሆኑት የምስል ማጣርያዎችን ተጠቅሜ አላውቅም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል (ከአንድ በላይ ድምፅ እንዲሰጥ ስለተደረገ ድምሩ ከ100% ይበልጣል)።

በአጠቃላይ 416 ሰዎች ድምፅ በመስጠት ተካፍለዋል።

መረጃዎችን እንዲሁም ምስሎችን ለማጣራት የሚረዱ የተለያዩ የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች ይገኛሉ። ከድረ- ገጾች እስከ ሞባይል መተግበሪያዎች ድረስ አይነታቸው ብዙ የሆኑ የመረጃ ማጣራትን ስራ የሚያቀሉ እና እውነተኝነታቸውን የሚያረጋግጡ መሳሪያዎች አሉ። ከእነሱም መካከል ዛሬ ቲንአይ(TinEye) የተባለውን እናስተዋውቃችሁ።

ይህ መተግበሪያ ምስሎችን በኢንተርኔት አማካኝነት ለማጣራት የሚጠቅመን ድረ-ገጽ ነው። የምንፈልገው ምስል ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ ውሎ ከነበረ መቼ እና የት እንዲሁም በምን መልኩ ጥቅም ላይ እንደዋለ ያሳውቀናል።

በዚህ መተግበርያ በፎቶሾፕ የተነካኩ ምስሎችንም ፈልጎ ማግኘት ይቻላል። ድረ-ገፁ www.tineye.com ሲሆን አጠቃቀሙ ደግሞ ድረ-ገጹ ላይ የምንፈልገውን ምስል ከኮምፒተር ወይም ከስልካችን ላይ መርጠን በማስገባት መፈለግ ነው። ያስገባነውን ምስል አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም ቲንአይ ከኢንተርኔ ላይ ከወሰዳቸው 45 ቢሊዮን ምስሎች ውስጥ ይፈለግለናል።

ምስሉን እና ምስሉን የሚመስሉ በርካታ ውጤቶችን ያወጣል፣ ከወጡት ምስሎች ውስጥም የምንፈልገውን መርጠን ስንመለከት ከዚህ በፊት ይህ ምስል የት ጥቅም ላይ እንደዋለ ማየት እንችላለን። ምንም ውጤት ካልመጣ ደግሞ ምስሉ ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ አልዋለም ማለት ነው፣ ወይም ምስሉ የቲንአይ ክምችት ውስጥ የለም ማለት ነው። ይህን መሳሪያ በነጻ መጠቀም መቻሉ አንዱ ጥሩ ጎኑ ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::