ይህ ምስል አዲስ ነው ወይስ የቆየ?

getachew reda

መጋቢት 19፣ 2015 ዓ.ም

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ በአንድ ላይ የሚታዩበት ይህ ምስል ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት እየተጋራ ይገኛል።

የዚህ ምስል መሰራጨትን ተከትሎ ግን አንዳንዶች “የቆየ ምስል” ነው ብለው አስተያየት የሰጡ ሲሆን ሌሎች ደግሞ የቅርብ ግዜ እንደሆነ ለማስረዳት ሲሞክሩ አስተውለናል፣ በርካታ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮችም ጉዳዩን እንድናጣራ ጥያቄ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ ቼክ የዚህን ምስል ጉዳይ በተመለከተ መረጃዎችን አሰባስቧል።

በዚህም መሰረት ስማቸው እንዳይጠቀስ ከጠየቁ ሁለት ሰዎች ባገኘው መረጃ ፎቶው ከሶስት ቀናት በፊት መጋቢት 16/2015 በአዳማ ከተማ ከነበረ ፕሮግራም ላይ የተወሰደ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።

ፕሮግራሙ በሰሜኑ ጦርነት በተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ግንባታ ዙርያ ክልሎች እና የፌደራል መንግስት ሊኖራቸው ስለሚገባ ሚና ውይይት የተደረገበት እንደነበር፣ የአማራ እና የአፋር ክልሎች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ተወካዮችም ተገኝተውበት የነበረ እንደሆነ ኢትዮጵያ ቼክ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።

አቶ ጌታቸው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መጋቢት 14/2015 በጠ/ሚር አብይ አህመድ መሾማቸው ይታወሳል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::