“ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ ጉንፋን መሰል ምልክቶች ጨምረዋል፣ ከኮቪድ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማወቅ ጥናት እየተደረገ ነው”— የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ቼክ

"ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ ጉንፋን መሰል ምልክቶች ጨምረዋል፣ ከኮቪድ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማወቅ ጥናት እየተደረገ ነው"--- የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ቼክ

መስከረም 22፣ 2016

ከሰሞኑ በርካታ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮች ጉንፋን መሰል ሳል እያጋጠማቸው እንደሆነ፣ ምናልባትም ኮቪድ ሊሆን እንደሚችል ስጋት እንደገባቸው ለኢትዮጵያ ቼክ ጠቁመው ከመንግስት ማብራርያ እንድናቀርብ ጠይቀውናል።

በዚህ ዙርያ ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ መረጃ ጠይቀናል። ዶ/ር ሊያ ይህን ምላሽ ሰጥተውናል:

“ሰሞንኛውን የጉንፋን መሰል ምልክት፣ እንዲሁም ምናልባት የኮቪድ መከሰት አመላካች ሊሆን የሚችሉ ምልክቶችን በቅርበት እየተከታተልነው ነው። ከበርካታ ስፍራዎች ናሙናዎችን ወስደን ምርመራ እያደረግን እንገኛለን። ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ ጉንፋን መሰል ምልክቶች ጨምረዋል፣ የጉንፋን ወቅት ደግሞ እየመጣ ነው። ባለፈው ሳምንት በነበረን መረጃ 2.5 ፐርሰንት የኦንፍሉዌንዛ እንዲሁም የ3 ፐርሰንት ኮቪድ ኬዞች ተመዝግበዋል። ነገር ግን የኮቪድ ኬዞች በፍጥነት እየጨመሩ አይደለም፣ የሆስፒታል ታማሚዎች ቁጥር ባለበት ነው። አሁንም በትንፋሽ አማካኝነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል ዋናው ትኩረታችን የግል ንፅህናን በመጠበቅ ነው፣ የኮቪድ ክትባት የሚያስፈልጋቸውም ክትባቱን ወስደው ከበሽታው ራሳቸውን እንዲጠብቁ እንመክራለን።”

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::