ሜታ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል መሪ ጄነራል መሐመድ ዳጋሎን እና የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉን ኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገጾች ማስወገዱን አስታወቀ

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ነሐሴ 12፣ 2015 ዓ.ም

  1. ሜታ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል (RSF) መሪ ጄነራል መሐመድ ሃንዲት ዳጋሎን እና የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉን ኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገጾች ማስወገዱን አስታወቀ። ገጾቹ እንዲወገዱ የተደረጉት የነውጠኛ ቡድኖችን እና ግለሰቦችን በሚገዛው የፌስቡክ ፖሊሲ መሰረት መሆኑ ተገልጿል። ሜታ ከሁለቱ ገጾች በተጨማሪ ከፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሌሎች ገጾች ማገዱ ተነግሯል።
  1. ዩቱብ ከህክምና ጋር የተገናኙ ሀሠተኛ መረጃዎችን ለመከላከል በፖሊሲዎቹ ላይ ጠንከር ያለ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል። ማሻሻያው ከአለም ጤና ድርጅትና ከየሀገራቱ የህክምና መመሪያዎች በተጻራሪ የሚጋሩ ይዘቶችን እንዲወገዱ ያደርጋል። ማሻሻያው በሽታን በመከላከል፣ በሽታን በማከም እና በሽታዎችንና ህክምናቸውን በመካድ ላይ የሚያተኩሩ ይዘቶችን በጥብቅ ይቆጣጠራል ተብሏል። ከካንሰር በሽታ ጋር በተገናኘ የተሰራጩ ሀሰተኛ ይዘቶችንም በሚቀጥሉት ቀናት በስፋት እንዲወገዱ እንዲወገዱ እንደሚያደርግ ዩቱብ አስታውቋል።
  1. የኬኒያ ፓርላማ ቲክቶክ እንዲታገድ የቀረበለትን አቤቱታ ባሳለፍነው ማክሰኞ መመልከቱን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። የቀረበው አቤቱታ በቲክቶክ የሚጋሩ ይዘቶች የኬኒያን ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴቶች የሚሸረሽሩ ስለመሆናቸው አጽኖት መስጠቱ ተዘግቧል። ፓርላማው በአቤቱታው ላይ ሞቅ ያለ ክርክር ያደረገ ሲሆን የፓርላማው አፈጉባዔ ሞሰስ ዋንታንጉላ በቲክቶክ የሚጋሩ ቪዲዮዎች መረን የለቀቁ ጾታዊ ይዘት ያላቸው ሁከትና ጥላቻን የሚያበረታቱ መሆናቸው በመግለጽ አቤቱታውን መደገፋቸው ተነግሯል። ፓርላማው በቀረብ አቤቱታ ላይ ውሳኔ አለመስጠቱም ተዘግቧል።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን በማህበራዊ ሚዲያ ስለሚታዩ አሉታዊ መስተጋብሮች በትግረኛ ጽሁፍ አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2131

-በጄነራል ጻድቃን ገ ትንሳኤ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንትን አጋልጠናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2133

-በአማራ ክልል በተከሰተው ግጭት በቁጭር ስር የዋሉ የጦር መሳሪያዎችን ያሳያሉ ተብለው የተሰራጩ ምስሎችን ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2135

-በአቶ ጌታቸው ረዳ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንትን አጋልጠናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2136

-ቴሌ ብርን በመምሰል በቴሌግራም አማካኝነት እየተፈፀመ የሚገኝ የማጭበርበር ድርጊት የተመለከተ መረጃ አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2138

-አርቲስት ቴዲ አፍሮ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መልዕክት እንዳስተላለፈ ተደርጎ የተሰራጨ ሀሰተኛ ደብዳቤ አጋልጠናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2139

-ከሰሞኑ በአማራ ክልል ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ የተጋራን ቪዲዮ ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2141

https://t.me/ethiopiacheck/2142

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::