በአማራ ክልል በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ከሳምንቱ አጋማሽ ጀምሮ የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ሐምሌ 28፣ 2015 ዓ.ም

  1. በአማራ ክልል በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ከሳምንቱ አጋማሽ ጀምሮ የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ሚዲያዎች ዘግበዋል። የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎቱ የተቋረጠው በክልሉ ከተፈጠረው አለመረጋጋትና ግጭት ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል በዘገባዎች ተጠቅሷል። ድርጊቱን ተከትሎም የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ የሲቪክ ድርጅቶች ትችት ሰንዝረዋል። የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በአማራ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ማረጋገጥ መቻሉን አመልክቶ ‘’የኢንተርኔት ግንኙነትን ማቋረጥ ግጭቶችን ለመከላከል እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን አይበጅም’’ ሲል እገዳው እንዲነሳ ጥሪ አቅርቧል።
  1. ኤክስ (X) የሰማያዊ ባጅ ተጠቃሚ ደንበኞቹን ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ መታወቂያ መጠየቅ ሊጀምር መሆኑን በማህበራዊ ሚዲያ መገናኛ ዘዴዎች ላይ አትኩሮ የሚዘግበው ሶሻል ሚዲያ ቱደይ ድረገጽ አስነብቧል። ኤክስ አሰራሩን ለመጀመር ወደ ሙከራ መግባቱ የተዘገበ ሲሆን የሰማያዊ ባጅ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ለማግኘት ማንነታቸውን የሚያሳይ የመንግስት መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ተብሏል። ኤክስ ከወራት በፊት የሰማያዊ ባጅ ምልክትን በሽያጭ ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ በርከት ያሉ ሀሰተኛ አካውንቶች ምልክቱን ስለመግዛታቸው በስፋት ሲነገር ቆይቷል።
  1. ሜታ አሉታዊ ይዘቶችን የሚከታተሉና የሚቆጣጠሩ ሰራተኞችን መቀነሱ ለሀሠተኛ መረጃና ለአሉታዊ መልዕክቶች ስርጭት በር ከፍቷል ተባለ። ኢንተርኒውስ የተባለ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ልማት ተቋም በሳምንቱ አጋማሽ ባወጣ ረዘም ያለ ሪፖርት የሜታ ድርጊት የኩባንያውን የይዘት ተከታታይና ተቆጣጣሪ ክፍል ስራ እንዲሽመደምድ አድርጎታል ብሏል።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን ሀሳብን የምግለጽ መብት ድንበር የት ድረስ መሆን ይገባል በሚል ርዕስ ጽሁፍ አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2106

-“ብድርን በቀላሉ ያግኙ” በማለት ማስታወቂያ በሚያስነግሩ የፌስቡክ ገጾች ላይ ፍትሻ አድርገናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2107

-የሴኔጋሉ ፕሬዝደንት ስለ ኤርትራ ተናገሩ ተብሎ በተሰራጨ መረጃ ላይም ማጣራት አድርገናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2111

https://t.me/ethiopiacheck/2112

-የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዕጣን በተመለከተም ማብራሪያ አስነብበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2114

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::