በፈጣን መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎች በሚጋሩ አሉታዊ ይዘቶች ተጋላጭ ላለመሆን ማድረግ የሚገባንጥንቃቄ

twitter verification

ሐምሌ 03፣ 2015

ከማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ መተግበሪያዎች  በተጨማሪ ብዙዎቻችን እንደ ቴሌግራም፣ ዋትስአፕ እናሲግናል ያሉ የፈጣን መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎችን በስፋት እንጠቀማለን። እነዚህን መተግበሪያዎችበተለይም ከወዳጆቻችን እና ከስራ ባልደረቦቻችን ጋር ግላዊ መረጃዎችን በቀላሉና ሚስጢራዊ በሆነ መንገድ(encrypted) ለመለዋወጥ እንመርጣቸዋለን። በዚህ ረገድ በሀገራች በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለውንቴሌግራም መጥቀስ ይቻላል።

ቴሌግራም መልዕክቶችን ሚስጢራዊ በሆነ መንገድ ለመለዋወጥ አዎንታዊ አገልግሎት ቢኖረውም በአንጻሩለሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች፣ ለጥላቻ መልዕክቶች እንዲሁም ለማጭበርበር ድርጊት ፈጻሚዎች የተመቸመሆኑን በቀላል ማስተዋል ይቻላል። ለዚህ ደግሞ የኩባንያዎ ለቀቅ ያለ ቁጥጥርና ክትትል አይነተኛ ሚናእንዳለው ብዙዎች ይጠቅሳሉ። ይህም እንደ ፌቡክ፣ ትዊተር፣ ዩቱብ ባሉ የማህበራዊ ሚድያዎች የማይፈቀዱአሉታዊ ይዘቶች ዋነኛ መናህሪያ አድርጎታል።

ከሀሠተኛና ከተዛቡ መረጃዎች፣ ከጥላቻ መልዕክቶች፣ ከማጭበርበር ድርጊቶች በተጨማሪም ለማየት የሚረብሹየስቃይና የግድያ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በስፋት ይጋሩበታል። ይህም በተለይ በተደጋጋሚ ሲሆን በተመልካቾችዘንድ የአዕምሮ መረበሽ እንደሚፈጥ ይታመናል።

ስለሆነም እንደ ቴሌግራም ባሉ የፈጣን መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎች በሚጋሩ አሉታዊ ይዘቶችተጋላጭ ላለመሆነ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። ለዚህም የምንከተላቸው ቻናሎችናየምንቀላቀላቸውን ግሩፖች በጥንቃቄ መምረጥ ይኖርብናል። ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሠተኛ ቻናሎችንመለየትና እራሳችንን ማራቅም ጠቃሚ ነው።

ምንም እንኳ ቴሌግራም አሉታዊ ይዘቶችን በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ ለቀቅ ያለ እንደሆን ቢታመንምሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን፣ የጥላቻ መልዕክቶችን፣ የማጭበርበር ድርጊቶችን እንዲሁም መንፈስን የሚረብሹፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን ስንመለከት ሪፖርት ከማድረግ ወደኃላ ማለት የለብንም። በተደጋጋሚ ሪፖርት ማድረግውጤት ሊያመጣ ይችላልና!

በቴሌግራም የሚሰራጩ ኣአሉታዊ ይዘቶችን ሪፖርት ለማድረግም የሚከተሉትን ሂደቶች ይከተሉ:

በመጀመሪያ ሪፖርት ማድረግ የፈለጉትን ቻናል ወይም ግሩፕ ይምረጡ፤

ቀጥሎ ከቻናሉ ወይም ከግሩፑ በስተቀኝ የሚገኙትን ሶስት ነጠብጣቦች (…) ይጫኑ፤

ከዛም ለምን ሪፖርት እንደሚያደርጉ ይምረጡ፤

በጨረሻምሪፖርትየሚለውን ይጫኑ።

በፈጣን መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎች በሚጋሩ አሉታዊ ይዘቶች ተጋላጭ ላለመሆን ጥንቃቄ እናድርግ!!

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::