ጎግል ዜና የሚጽፍ የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ ወደስራ ለማስገባት ሙከራ ማድረግ መጀመሩ ተገለጸ

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ሐምሌ 14፣ 2015

  1. ጎግል ዜና የሚጽፍ የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ ወደስራ ለማስገባት ሙከራ ማድረግ መጀመሩን ዘ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በሳምንቱ አጋማሽ ዘግቧል። ጎግል ቴክኖሎጅውን በተመለከተም ለዋሽንግተን ፖስት፣ ለዘ ኒውዮርክ ታይምስ እና ለዋል ስትሪት ጆርናል ባለቤት ኒውስ ኮርፕ ገለጻ መስጠቱ በዘገባው ተካቷል። ዜና ጸሃፊ የሰው ሰራሽ አስተውሎቱ ጋዜጠኞች እንደማይተካ ይልቁንስ ረዳት በመሆን ስራቸው እንደሚያቃልል እና በምላሽ ሰጭ የሰውሰራሽ አስተውሎት (Generative AI) ቴክኖሎጅዎች የሚፈረኩ ሀሠተኛ ዘገባዎችን ለመለየት እንደሚረዳም ጎግል ማብራራቱን ጋዜጣው አስነብቧል። ለጋዜጣው አስተያየታቸውን የሰጡ የሚዲያ ባለሙያዎች በበኩላቸው ቴክኖሎጅው አውድን የመረዳት አቅሙን እንደሚጠራጠሩ አስረድተዋል።
  1. በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሠተኛ መረጃዎችና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶች በዜጎች ላይ ፍርሃትና ሽብር ፈጥረዋል ሲሉ የኬኒያ ወንጀል ምርመራ ዳሬክቶሬት ሃላፊ ሞሃመድ አሚን በሳምንቱ አጋማሽ መግለጻቸውን ካፒታል ኤፍኤም ዘግቧል። ሃላፊው መስሪያ ቤታቸው ድርጊቱን በአጽኖት እየተከታተለው መሆኑን ገልጸው ሀሠተኛ መረጃዎችና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን የሚያሰራጬ አካላት እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል። ባለፉት ቀናት በኬኒያ በተከሰተው ተቃውሞ እና አለመረጋጋት በርከት ያሉ ሰዎች መሞታቸው ይታወቃል።
  1. በኢትዮጵያ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ለወራት ተጥሎ የቆየው እገዳ በሳምንቱ መጀመሪያ መነሳቱን ተመልክተናል። ከየካቲት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ዩትዩቱብ፣ ቴሌግራም እና ሜሴንጀር መተግበሪያዎች ላይ እገዳ ተጥሎ መቆየቱ ይታወቃል። አብዛኛው ተጠቃሚም በቪፒኤን (VPN) አማካኝነት አገልግሎቶችን ሲያገኝ መቆየቱ ይታወቃል።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ ስለደቀነው ስጋት በአፋን ኦሮሞ ጽሁፍ አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2086

– በኢትዮጵያ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ለወራት ተጥሎ የቆየው እገዳ ስለመነሳቱ የሚገልጽ ዘገባም አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2088

– “ሶሻል ሚድያ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሚና ምን ያህል ነው?” በሚል ባቀረብነው መጠየቅ ያገኘነውን ምላሻም አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2089

– የወረታ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ተገደሉ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ስለተለቀቀው መረጃ የወረታ ከተማ አስተዳደር የሰጠውን ምላሽ አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2090

– ከአውድ ውጭ የተወሰዱ ምስሎችን ለመለየት ስለሚረዱ ፍንጮች የሚያስረዳ ጽሁፍም አስነብበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2091

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::