የሰውሰራሽ አስተውሎት ስጋትን ለመቀነስ የተቀናጀ አለም አቀፍ ምላሽ እንዲኖር የተመድ ዋና ጸሃፊ ጥሪ አቀረቡ

UNESCO urges tougher regulation of social media

ሰኔ 09፣ 2015 ዓ.ም

  1. በዲጂታል ሚዲያዎች የሀሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ መልዕክቶች ማሻቀብን እንዲሁም የሰውሰራሽ አስተውሎት ስጋት ለመቀነስ የተቀናጀ አለም አቀፍ ምላሽ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዋና ጸሃፊው በሳምንቱ መጀመሪያ አስታውቀዋል። መንግስታትን፣ የቴክኖሎጅ ኩባንያዎችና የማስታወቂያ አስነጋሪዎችን የሚገዛ የስነምግባር መርህ (cond of conduct) ማርቀቅ ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ጉዳዩን የሚመለከት ሳይንሳዊ አማካሪ ቦርድ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚያዋቅሩ የተናገሩት ጉቴሬዝ የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ ስጋትን ለመቆጣጠር የአለም አቀፉን የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲን መሰል ተቋም እንዲመሰረት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
  1. ዩቱብ ይዘት ፈጣሪዎች በማስታወቂያ ገቢ ወደ ሚያገኙበት መርሃግብር (monetization) የሚቀላቀሉበትን መስፈርት ቀለል ማድረጉን አስታውቋል። በአዲሱ መስፈርት መርሃግብሩን ለመቀላቀል 500 ደንበኛ (subscribers) ማፍራት፣ 3 ቪዲዮዎች መጫና፣ በአንድ አመት ውስጥ 3000 የእይታ ሰዐት ማከማቸት ወይም በ90 ቀናት ውስጥ 3 ሚሊዮን የአጭር ቪዲዮ እይታ ማስመዝገብ ይጠብቅባቸዋል። ከዚህ ቀደም መርሃግብሩን ለመቀላቀል 1000 ደንበኛ ማፍራት፣ 4000 የእይታ ሰዐት ማከማቸት ወይም በ90 ቀናት ውስጥ 10 ሚሊዮን የአጭር ቪዲዮ እይታ ማስመዝገብ ይጠበቅባቸው ነበር። የመስፈርቱ መላላት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ፈጻሚዎችን ቁጥር ያንረው ይሆናል የሚል ስጋት ማጫሩን ተመልክተናል።
  1. ትዊተር የሰማያዊ ባጅ ደንበኞቹ (Twittet Blue Subscribers) ይዘት ካጋሩ በኃላ አርትዖ (edit) መከወን የሚችሉበትን የጊዜ ገደብ ወደ አንድ ሰዐት ማራዘሙን አስታወቀ። ትዊተር የአርትዖ ቁልፍን በያዝነው አመት መጀመሪያ ለባለሰማያዊ ባጅ ደንበኞቹ ብቻ መክፈቱ የሚታወስ ሲሆን ይዘቶች ከተጋሩ በኃላ አርትዖ ለመከወን የጊዜ ገደቡ ደቂቃ ብቻ ነበር።

✅️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች ትክ ክለኛነት ማረጋገጫ ባጅ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል የሚያስረዳ ጽሁፍ በትግረኛ አጋርተናል: https://t.me/ethiopiacheck/2031

-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከደንበኞች ሂሳብ ላይ ስለሚደረግ ስርቆት ያጋራውን መረጃ በአማርኛና በትግረኛ አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2033

https://t.me/ethiopiacheck/2034

-የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቆን የተመለከቱ የቲክቶክ ቪዲዮዎችንም ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2035

https://t.me/ethiopiacheck/2036

 

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::