ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎች በአዳጊው የጋና ዴሞክራሲ ላይ ስጋት ደቅኗል ተባለ

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

መስከረም 11፣ 2016 ዓ.ም

  1. ቲክቶክ በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ የሚሰሩ ይዘቶች የሚለይና ምልክት የሚያስቀምጥ አጋዥ መገልገያ ወደስራ ለማስገባት መዘጋጀቱን ባሳለፍነው ማክሰኞ አስታውቋል። አጋዥ መገልገያው በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ የተሰሩ ይዘቶችን በቀላሉ ይለያል ተብሏል። ቲክቶክ ዲፕፌክን ጨምሮ በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ በሚሰሩ ይዘቶች አንጻር እስከ ክልከላ የሚደርስ ጠበቅ ያለ ፖሊሲ እንዳለው ይታወቃል።
  1. ሜታ ፌስቡክና ኢንስታግራም ለሚጠቀሙ ተቋማትና ድርጅቶች ሰማያዊ ባጅ መሸጥ መጀመሩን አስታውቋል። ሰማያዊ ባጁ የተቋማትና ድርጅቶቾን የእይታ መጠን እንደሚጨምር እንዲሁም ተመሳስለው የሚከፈቱ ኣአካውንቶችን በቀላሉ ለመለየት እንደሚያስችል ሜታ ገልጿል። ሜታ የግል አካውንት ላላቸው ደንበኞቹ ቀደም ብሎ ሰማያዊ ባጅ መሸጥ መጀመሩ ይታወቃል።
  1. የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ማሻቀብ በማድግ ላይ ያለውን የጋና ዴሞክራሲያዊ ስርዐት ያናጋዋል የሚል ፍርሃት እንዳሳደረባቸው የሀገሪቱ የኮሚኒኬሽን ሚንስትር በዛሬው ዕለት አስታውቀዋል። ሚንስትር ኮጆ ኦፖንግ ንኩሩማኸ ሚዲያዎች ችግሩን ለመከላከል ያሳዩት ተለሳላሽነት ይብልጥ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን በማሰራጨት በኩልም ሁሉም የፖለቲካ ወገኖች ተሳታፊ መሆናቸውን አብራርተዋል።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው፥

– በሰኞ መልዕክታችን የሚዲያ አጠቃቀም ንቃትን የተመለከተ ጽሁፍ አጋርተናል:https://t.me/ethiopiacheck/2188

-በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተቃውሞ ሰልፍ ስለመደረጉ የቀረበን ኣአሳሳች ምስል አጋልጠናል:https://t.me/ethiopiacheck/2190

-የጥላቻ መልዕክቶችን ስርጭት ለመከላከል ሊኖረን ስለሚገባ አስተዋጾ የሚያስረዳ ጽሁፍም አቅርበናል:https://t.me/ethiopiacheck/2191

-እንዲሁም የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን ከአዕምሮ ጤና አንጻር የሚቃኝ መልዕክትን አጋርተናል:https://t.me/ethiopiacheck/2192

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::