36 የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች የጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት እንዲቆም ጠይቀዋል

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ጷጉሜ 03፣ 2015 ዓ.ም

  1. 36 የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች የጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት እንዲቆም አዲሱን ዓመት አስመልክተው በሳምቱ አጋማሽ ባቀረቡት የሰላም ጥሪ ጠይቀዋል። ድርጅቶቹ ባቀረቡት ጥሪም “የጥላቻ ንግግሮች እና ግጭት ቆስቋሽ መልዕክቶች ነውጥ አዘል ግጭቶችን የሚያዋልዱ እና የሚያፋፍሙ መሆናቸውን ባለፉት ዓመታት አስተውለናል” ያሉ ሲሆን የማኅበራዊ ሚዲያ አቀንቃኞች እና ሌሎችም የተዛቡ መረጃዎችን ከማሰራጨት፣ ብሎም ሕዝብን በጅምላ ከሚፈርጁ ወይም ግጭቶችን ከሚቆሰቁሱ እና ከሚያባብሱ የቋንቋ አጠቃቀሞች እና መልዕክቶች ራሳቸውን እንዲቆጥቡ” አሳስበዋል።
  1. ዩቱብ በዩናይትድ ኪንግደም ለሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች የብቃት ማረጋገጫ ባጅ መስጠት መጀመሩን ቢቢሲ ዘግቧል። የብቃት ማረጋገጫ ባጁ በዩቱብ የሚሰራጩ ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ለመከላከል ያለመ መሆኑ በዘገባው ተካቷል። ዶክተሮች፣ ነርሶችና የሰነልቦና ባለሙያዎችም የብቃት ማረጋገጫ ባጁን ለማግኘት ካሳለፍነው ሰኔ ጀምሮ መመዝገብ መጀመራቸው ተገልጿል። ከምዝገባው መስፈርቶች መካከልም የህክምና ሙያ ፈቃድና ከዚህ በፊት ሀሰተኛና የተዛባ ይዘት ያላቸውን መረጃዎች አለማሰራጨት ተጠቅሰዋል። ባጁን የሚያገኙ ባለሙያዎች የሚያጋሩት ይዘት ቅድሚያ እንዲታይ እንደሚደረግም ተገልጿል። ዩቱብ ህክምና ነክ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ለመቆጣጠር እንዲረዳው በፖሊሲዎቹ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ከሳምንታት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል።
  1. ጎግል በፍለጋ ውጤቶች ግርጌ በሚያሳያቸው ቅምሻዎች (Snippets) ውስጥ የዜና እና የሌሎች ይዘቶችን ዘጋቢዎችንና ጸሐፊያን ስም ለማካተት ሙከራ መጀመሩን በቴክኖሎጅ ዙሪያ የሚዘግበው ሰራውንድቴብል አስነብቧል። ጎግል ከዚህ ቀደም በፍለጋ ቅምሻዎቹ የዜናውን ርዕስ፣ ምስል እና አንኳር ጉዳዩን ብቻ ያሳይ እንደነበር ይታወቃል። የዘጋቢዎችንና የጸሐፊያን ስም በቅምሻ ውስጥ እንዲካተት መደረጉ አንባቢያን የተሻለ መረጃን ለማግኘት ይበልጥ ያግዛል ተብሏል።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው፥

– በሰኞ መልዕክታችን በማህበራዊ ሚዲያ ስለሚጋሩ ጤና ነክ መረጃዎች ማድረግ ስላለብን ጥንቃቄ በትግረኛ አስነብበናል: https://t.me/ethiopiacheck/2169

– በኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ስም የተከፈተን ሀሠተኛ የቴሌግራም ቻናልም አጋልጠናል:https://t.me/ethiopiacheck/2172

-በማህበራዊ ሚዲያ በሚጋሩ ይዘቶች ስር የሚጻፉ አስተያየቶችን ማንበብ እውነተኛ መረጃን ለማግኘት የሚኖረው አስተዋጾ የተመለከተ ማብራሪያም አጋርተናል:https://t.me/ethiopiacheck/2173

https://t.me/ethiopiacheck/2174

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::