በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ላይ የሚደረግ የማበልጸግ ስራ ገታ እንዲደረገ ደብዳቤ ተሰራጨ፣ እና ሌሎች መረጃዎች

UNESCO urges tougher regulation of social media

መጋቢት 22፣ 2015 ዓ.ም

  1. በፌስቡክና ኢንስታግራም የሚጋሩ ማስታወቂያዎች አሉታዊና ስሜት ቀስቃሽ ይዘት ካላቸው ልጥፎች (posts) አቅራቢያ እንዳይሆኑ የሚረዳ መገልገያ ወደስራ ማስገባቱን ሜታ አስታውቋል። አዲሱ መገልገያ በክፍያ የሚጋሩ ማስታወቂያዎች የጦር መሳሪያ፣ የፖለቲካ ክርክር ወዘተ ይዘት ካላቸው ልጥፎች በላይ፣ በታች፣ ወይም በታች እንዳይታዩ ይረዳል ተብሏል። በርካታ ማስታወቂያ አስነጋሪዎች ማስታወቂያቸው ከጥላቻ መልዕክቶች፣ ከሀሰተኛ መረጃዎችና ከሌሎች አሉታታዊ ይዘቶች አቅራቢ እንዳይታዩ ጉትጎታ ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሰራሩ ለጊዜው በእንግሊዘኛና በስፓኒሽ ቋንቋ የሚጋሩ ይዘቶችን የተመለከተ መሆኑም ተገልጿል።2. የጎግል ማሰሻ (Google Search) “እይታዎች” (Perspectives) እና “ስለጸሃፊው” (About this author) የተባሉ ሁለት አገልግሎቶችን በቅርቡ ወደስራ እንደሚያስገባ አስታወቀ። አገልግሎቶቹ የጎግል ማሰሻን በመጠቀም መረጃ የሚያፈልጉ ሰዎች ስለመረጃው የተሟላ አውድ እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል። “እይታዎች” የተሰኘው አገልግሎት ለመረጃ ፈላጊዎች የተለያየ እይታ ባላቸው ጸሃፊያን፣ ጋዜጠኞች፣ ተመራማሪዎች ወዘተ የተጻፉ ውጤቶችን የሚያቀር ሲሆን “ስለጸሃፊው” የተሰኘው አገልግሎት ደግሞ የጸሃፊውን ማንነት የሚያስረዳ ይሆናል ተብሏል።3. ኢሎን መስክን ጨምሮ ከ1000 ሺህ በላይ ተጽኖ ፈጣሪ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እንደ ቻትጂፒቲ (ChatGPT) ባሉ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎች ላይ የሚደረግ የማበልጸግ ስራ ገታ እንዲደረገ የሚጠይቅ ግልጽ ደብዳቤ በትናንትናው ዕለት አሰራጭተዋል። ፈራሚዎቹ አሰላሳይ በሆኑ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጅዎች ላይ የሚደረግ ተጨማሪ የማበልጸግ ድርጊት በሰው ልጆች ላይ አደጋ ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋታቸውን አስነብበዋል። ከስጋቶቹ መካከል ለሀሰተኛ መረጃና ፕሮፓጋንዳ ይውላሉ የሚለው ተጠቅሷል።

    ️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

    – በሰኞ መልዕክታችን ትዊተር የጀመረውን አዲስ የአካውንት ማረጋገጫ አሰራርን የተመለከተ ጽሁፍ አስነብበናል:
    https://t.me/ethiopiacheck/1936

    – ወደ አዲስ አበባ ገብቷል ተብሎ ስለተሰራጨ የእህል መጠንም ፍተሻ አድርገናል:
    https://t.me/ethiopiacheck/1940

    -በአሜሪካ ኢምባሲ ስም ስለተከፈተ ሀሰተኛ የቴሌግራም አካውንትም መረጃ አጋርተናል:
    https://t.me/ethiopiacheck/1941

    -የቆየ ነው ተብሎ የተሰራጨ ፎቶ ላይም ማጣራት አድርገናል:
    https://t.me/ethiopiacheck/1942

    -በተመሳሳይ የአሁን ነው ተብሎ በትዊተት በተጋራ ቪዲዮ ላይም ፍተሻ አድርገናል:
    https://t.me/ethiopiacheck/1943

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::