ፈረንሳይ ዕጬ ተወዳዳሪዎች ከምርጫ ቀን በፊት ባሉት ስድስት ወራት የትዊተርን ሰማያዊ ባጅ መጠቀም እንደማይችሉ አስታወቀች

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ሐምሌ 21፣ 2015

  1. ፈረንሳይ ዕጬ ተወዳዳሪዎች ከምርጫ ቀን በፊት ባሉት ስድስት ወራት የትዊተርን ሰማያዊ ባጅ መጠቀም እንደማይችሉ አስታወቀች። የሀገሪቱ የፖለቲካ ፋይናሶች ተመልካች ኮሚሽን (CNCCFP) በትዊተር ገጹ ባስነበበው ረዘመ ያለ ጽሁፍ በክፍያ የሚገኘው ሰማያዊ ባጅ የፈረንሳይን የምርጫ ህግ እንደሚጥስ አብራርቷል። የፈረንሳይን የምርጫ ህግ ከምርጫ ቀን በፊት ባሉት ስድስት ወራት በክፍያ የሚደረጉ የሚዲያ ቅስቀሳዎችን ይከለክላል።
  1. አጫጭር ቪዲዮዎችን ለማጋራት በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ የሆነው ቲክቶክ ደንበኞቹ ጽሁፍ ማጋራት የሚችሉበትን አዲስ አሰራር ወደስራ ማስገባቱን አስታውቋል። አዲሱ አገልግሎት ደንበኞቹ ሀሳባቸውን የሚገለጹባቸውን አማራጮች ያሰፋል ሲል ቲክቶክ እንደሚሆን ቲክቶክ በሳምንቱ መጀመሪያ ባጋራው ብሎግ አስነብቧል።
  1. ትዊተር ስሙንና የንግድ ምልክቱን ወደ ኤክስ (X) መቀየሩን በሳምንቱ መጀመሪያ አስታውቋል። በዚህም በትዊተር መለያነት የምቻወቀው ነጭ ወፍ በ ‘X’ ተተክታለች። የስምና የንግድ ምልክት ቅያሬው የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ፕላትፎርሙን ወደ ሁሉን አቀፍ መተግበሪያ (the everything app) የመቀየር አካል መሆኑን የኩባንያው ባለቤት ኢሉን መስክ አስታውቋል።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅን የተመለከተ ጽሁፍ በትግርኛ አስነብበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2093

– እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል ተብሎ የተሰራጨን መረጃን አጣርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2095

– በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት የተሰራጨ ቪዲዮንም ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2099

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::