“የወረታ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ተገደሉ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው ሃሰተኛ መረጃ ነው”—- የወረታ ከተማ አስተዳደር

ሐምሌ 13፣ 2015

በትናንትናው እለት ማለትም ሃምሌ 12/2015 .  በባህር ዳር ከተማ የቀድሞ ፖሊስ አባል የነበሩና ጡረታየወጡና በንግድ ስራ የተሰማሩት አቶ መልኬ ጤናው የተባሉ ግለሰብ ድንገተኛ ግድያን ተከትሎ የተሳሳተና ከእውነት የራቀ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቶ ነበር።

በዚህም መሰረት የወረታ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ተገደሉ ተብሎ የተለቀቀው መረጃ ከእውነት የራቀና የተሳሳተ መረጃ መሆኑንና የወረታ ከተማ ፖሊስ /ቤት ኃላፊም በአሁኑ ሰዓት በስራ ላይ ያሉና ስራቸውን እያከናወኑ ያሉመሆኑን የወረታ ከተማ አስተዳደር በፌስቡክ ገፁ ገልጿል።

አስተዳደሩ ህብረተሰቡ በሃሰተኛ መረጃ ከመደናገር እራሱን እይዲጠብቅ አሳስቧል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::