በዶ/ር አለሙ ስሜ ስም እና ምስል ከተከፈተ ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት እንጠንቀቅ

A fake Twitter account with the name and image of Dr. Alemu

የካቲት 26፣ 2015 ዓ.ም

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር በሆኑት በዶ/ር አለሙ ስሜ ስም እና ምስል የተከፈተ የትዊተር አካውንት በርካታ አነጋጋሪ መረጃዎችን እያሰራጨ እንደሆነ ተመልክተናል።

አካውንቱ ህዳር 2014 ዓ/ም ላይ የተከፈተ ሲሆን ኢትዮጵያ ቼክ በወቅቱ አካውንቱ ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጦ ነበር። በወቅቱም ዶ/ር አለሙ ስሜ አካዉንቱ የርሳቸዉ እንዳልሆነና ተመሳስሎ የተከፈተ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ ነግረው ነበር።

ይሁን እንጂ ይህ አካዉንት የተለያዩ መረጃዎችን ማሰራጨት ከመቀጨሉ በተጨማሪ አምና ታህሳስ ወር ላይ 650 የነበረዉ የተከታዮቹ ብዛት አሁን ላይ ከ10,000 በላይ ደርሷል።

ከትዊተር አካዉንቶች በተጨማሪ በርካታ የፌስቡክ አካዉንቶችና ገጾች የግለሰቡ ስምና ምስልን በመጠቀም መከፈታቸዉንም ተመልክተናል።

ይሁን እንጂ ዶ/ር አለሙ ስሜ አንድ የፌስቡክ ገጽ እንዳላቸዉ ገልፀውልናል: https://www.facebook.com/Dralemu.official/

ተመሳስለው የሚከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እና ቻናሎችን ባለመከተል ራሳችንን ከሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግሮች እንጠብቅ የሁልግዜ መልዕክታችን ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::