የዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነን ስምና ምስል በመጠቀም ከቀናት በፊት የተከፈተ የትዊተር አካውንት!

A Twitter account that was opened using the name and image of Dr. Wedajeneh Maharenen is faake

መጋቢት 4፣ 2015 ዓ.ም

የዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነን ስምና ምስል በመጠቀም ከቀናት በፊት የተከፈተ የትዊተር አካውንት መኖሩን ተመልክተናል።

አካውንቱ አሁን ላይ 741 ተከታዮችን ማፍራት የቻለ ሲሆን ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች ሲያጋራ አስተውለናል።

በዚህም በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብረ-መልሶችን በማግኘት ላይ ይገኛል።

ከላይ የተጠቀሰው አካውንት የእርሳቸው አለመሆኑን ዶር ወዳጄነህ ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቀዋል።

በተመሳሳይ የዶ/ር ወዳጄነህን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈተና አሁን ላይ ከ3,600 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽም የእርሳቸው አለመሆኑን የገለጹ ሲሆን በስማቸው የተከፈተ የትዊተርም ሆነ የፌስቡክ ገጽ እንደሌላቸውም አሳውቀዋል።

ዶ/ር ወዳጄነህ በተለያዩ ሚዲያዎችና መድረኮች በተለይም ማህበራዊና መንፈሳዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ አስተያየቶች በመስጠት ይታወቃሉ።

ተመሳስለዉ የተከፈቱ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና አካዉንቶች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ጥንቃቄ እናድርግ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::