በፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ዙርያ እየተሰራጨ የሚገኝ ሀሰተኛ መረጃ

Fake information is being spread around President Sahle Work's asylum

ህዳር 10፣ 2016 ዓ.ም

አንዳንድ የትዊተር አካውንቶች እና የፌስቡክ ገፆች ባሳለፍነው ሳምንት ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በአሜሪካ ጥገኝነት እንደጠየቁ የሚገልፁ መረጃዎችን ሲያጋሩ እንደነበር ተመልክተናል።

ይህን መረጃ ካጋሩት መሀል ‘AmharaAquila’ የሚል ስያሜ ያለው እና ከ12,700 በላይ ተከታታዮች ያሉት የትዊተር ሰማያዊ ባጅ ያለው አካውንት ይገኝበታል። አካውንቱ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ጥገኝነቱን የጠየቁት በሀገራቸው መንግስት መጥፎነት ምክንያት እንደሆነ መረጃ አጋርቷል።

በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ ማጣራት ያደረገ ሲሆን መረጃው የተሳሳተ እንደሆነ ታውቋል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፕሬዝደንት ፅ/ቤት ባልደረባ ርዕሰ ብሄሯ በስራቸው ላይ እንደሚገኙ አረጋግጧል። ይህንን የሚያረጋግጠው ሌላ ግልፅ መረጃም ርዕሰ ብሄሯ በትናንትና እለት የተከናወነውን የታላቁ ሩጫን ማስጀመራቸው ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ “The Imperative for Sustainable Industrial Development in Africa” በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክና UNDP ያዘጋጁትን 18ኛውን የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮንፈረንስ ባሳለፍነው ሳምንት ህዳር 6 በንግግር መክፈታቸውን ተመልክቷል፡፡

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::