“ይህ ሀሰተኛ አካውንት ነው፣ የኔን [ትክክለኛ] አካውንት ብዙ ጊዜ አሳውቄ ነበር”— ረ/ኮ ደራርቱ ቱሉ ለኢትዮጵያ ቼክ

fake-facebook-page-impersonating-ethiopian-athletics-federation-president-derartu-tulu-ደራርቱ-ቱሉ

ሚያዝያ 21፣ 2015

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጽሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨቱን ተመልክተናል።

ይህ ገጽ 79 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን በፕሬዝዳንቷ ስም ሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎችን ማጋራትከጀመረ ሰነባብቷል። ኢትዮጵያ ቼክም በተለያዩ ጊዜያት ስለዚህ ሀሰተኛ ገጽ የጥንቃቄ መረጃዎችን ሲያጋራቆይቷል።

ይሁን እንጂ ገጹ 18 እና 20 አመት በታች የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ ወደ ዛምቢያ ያቀናዉን የታዳጊና ወጣት ቡድን በተመለከተ ሀሰተኛ መረጃ አጋርቷል።

ቡድኑ ዛምቢያ ከደረሰ በኋላ መኝታ ከማጣት ጋር በተገናኘ እክል እንደገጠመው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።

ይሁን እና በረ/ኮሚሽነሯ ስም የተከፈተው ሀሰተኛ አካውንት ደራርቱ ቱሉ ጉዳዩን በተመለከተ ይቅርታ እንደጠየቀች በማስመሰል ሀሰተኛ መረጃ ጽፏል።

በመሪዎች ችግር በሃገሬ የማየው ምስቅልቅል እኔ በምመራው ተቋም ውስጥ ልጆቼ(አትሌቶች) እንዲህ በብርድ በየመንገዱ ኩርምት ብለው ሲዋረዱ በፍፁም ማየት አልሻምየሚልን ጨምሮ ሌሎች ሀሰተኛ መረጃዎችንበውስጡ ይዟል።

ይህን ሀሰተኛ መረጃም በርካታ ተከታዮች ያሏቸው ግለሰቦችን ጨመሮ 350 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ሲያጋሩት 450 በላይ ተጠቃሚዎች ደግሞ ሀሳብ እና አስተያየታቸውን ሰጥተዉበታል።

ይሁን እንጂ ገጹን እና የተጋራውን መረጃ በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ /ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ያናገረ ሲሆን ገጹም ሆነ እሷ እንደጻፈችው ተደርጎ የተጋራው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጣለች።

በተጨማሪምትናንት ምሽት ትንሽ ያልተመቻቸ ነገሮች ልጆቻችንን ንዶላ ከተማ (ዛምቢያ) አጋጥሟቸው ነበር፣ለሌላ ስራ እኔ ሉሳካ ከተማ ነበርኩ። ይሁንና ተከስቶ የነበረው ችግር አሁን ተፈቷል፣ ልጆቻችንም ወደ ሉሳካተመልሰዋል። የተወሰኑት በዛሬው እለት ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉብላለች።

/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ትክክለኛነቱ የረጋገጠ (verified) የፌስቡክ ገጽ ያላት ሲሆን እሱም በዚህ ማስፈንጠሪያይገኛል: https://www.facebook.com/derartutulugemechu?mibextid=LQQJ4d

ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና አካውንቶችን ብቻ በመከተል ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎችእንዳንጋለጥ ጥንቃቄ እናድርግ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::