ለሀሰተኛ መረጃ መስፋፋት አስተዋጽኦ ከሚያደርጉት መሀል የቱ ሊጠቀስ ይችላል?

Factors that contribute to the spread of false information

ግንቦት 19፣ 2015 ዓ.ም

በትናንትናው እለት “ለሀሰተኛ መረጃ መስፋፋት አስተዋፅዖ ከሚያደርጉት መሀል የቱ ሊጠቀስ ይችላል?” የሚል ጥያቄን ኢትዮጵያ ቼክ ለተከታታዮቹ ቴሌግራም ላይ አቅርቦ ነበር።

ለዚህ ጥያቄ የቀረቡት አማራጮች፥

  1. 1. በማህበረሰቡ ዘንድ ዝቅተኛ የሚድያ አጠቃቀም ክህሎት መኖር
  2. 2. እንደ ግጭት እና ወረርሽኝ ያሉ ክስተቶች መኖር
  3. 3. በሀሰተኛ መረጃ ላይ የሚሰሩ ተቋማት አለመኖር ወይም ማነስ
  4. 4. የሚድያዎች ስርጭቱን በመከላከል ስራ ላይ አለመሳተፍ እንዲሁም
  5. 5. ሁሉም መልስ ነው የሚሉ ናቸው።

ለጥያቄው 525 ሰዎች ድምፅ የሰጡ ሲሆን በዚህም መሰረት 62% ሁሉም መልስ ነው፣ 16% በማህበረሰቡ ዘንድ ዝቅተኛ የሚድያ አጠቃቀም ክህሎት መኖር፣ 9% በሀሰተኛ መረጃ ላይ የሚሰሩ ተቋማት አለመኖር ወይም ማነስ፣ 7% የሚድያዎች ስርጭቱን በመከላከል ስራ ላይ አለመሳተፍ እና 6% እንደ ግጭት እና ወረርሽኝ ያሉ ክስተቶች ብለው ድምፅ ሰጥተዋል።

በርካቶች እንደመለሱት ሁሉም መልስ ናቸው።

ግጭቶች፣ አለመረጋጋቶች እንዲሁም ቀውሶች ለሀሰተኛ መረጃ መሰራጨት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ።

የፖለቲካ አለመረጋጋት ወይንም ግጭቶች ሲኖሩ ስለክስተቶቹ ለማወቅ ጉጉት ማሳደር ተፈጥሯዊ ነው።

በእንዲህ ያሉ ወቅቶች የሰበር ዜናዎች ቁጥር እና ድግግሞሽም ይጨምራል፣ ሁሉም ሰበር ዜናዎች እውነት ናቸው ማለት ግን አይደለም።

በአንጻሩ በርከት ያሉት ሰበር ዜናዎች የተሳሳቱ የመሆን እድላቸው ሰፊ መሆኑን ባለፉት ሳምንታት ብዙዎቻችን ታዝበናል።

ከዚህም በተጨማሪ የማህበረሰቡ ዝቅተኛ የሚድያ አጠቃቀም ክህሎት (media literacy rate) ለዚህ የተሳሳተ መረጃ ስርጭት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

እንደ ኢትዮጵያ ቼክ ያሉ ሌሎች በርካታ በመረጃ ማጣራት ስራ ላይ ያሉ ተቋማት አለመኖራቸው እና የሌሎች ሚድያዎች በስራው ላይ በንቃት አለመሳተፍ ችግሩ እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::