የዲጂታል ዕቁብ ዕጣ አወጣጥን የተመለከቱ ጥያቄዎች እና ያዘጋጀናቸው መልሶች

የዲጂታል ዕቁብ ዕጣ አወጣጥን የተመለከቱ ጥያቄዎች እና ያዘጋጀናቸው መልሶች

ሐምሌ 21፣ 2015

የዲጂታል ዕቁብ ዕጣ አወጣጥን የተመለከቱ ጥያቄዎች እና ያዘጋጀናቸው መልሶች

በቴሌብር ሱፐር አፕ አማካኝነትን የሚካሄደውን የዲጂታል ዕቁብ ዕጣ አወጣጥን የተመለከቱ ጥያቄዎችከኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮች ደርሰውናል።

ከጥያቄዎቹ መካከልዕቁብተኞች ተብለው ስማቸው የሚዘረዘሩት ሰዎች በርግጥም ስለመኖራቸው እና ዕጣወጣላቸው ተብለው ስማቸው የሚዘረዘሩት ሰዎች እውነተኛ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ መስጠት ላይ ግልጽነትያንሰዋልየሚሉ ይገኙባቸዋል።

ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን በተመለከተ የዲጅታል ዕቁቡን የሚስተዳድረውን ዲጂታል ዕቁብ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ /የተ/የግ/ማን እና ኢትዮቴሌኮምን ማብራሪያ ጠይቋል።

የዲጂታል ዕቁብ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ /የተ/የግ/ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ብስራት ፍቅሩ የዲጂታል ዕቁቡህጋዊ መሆኑን ገልጸው ከኢትዮቴሌኮም ጋርም የሚሰሩት ህጋዊ መሆናቸው ተረጋግጦና ውል ገብተው መሆኑንአብራርተዋል።

የዕቁቡ ደንበኞች ዕቁቡን ከመጀመራቸው በፊት ማንነታቸው ታውቆ እንደሚመዘገቡ የተናገሩት አቶ ብስራትየዕቁቡ ገንዘብ የሚሰበሰበውም ሆነ ዕቁብ ለሚደርሳቸው ሰዎች ክፍያ የሚፈጸመው ከሰው ንክኪ ውጭበቴሌብር አማካኝነት መሆኑንም አስረድተዋል።በሰዎቹ እውነተኛነት ጥርጣሬ ያላቸው ደንበኞች በአካል ቢሮመጥተው ዳታ ማየት እንዲሁም ከሌሎች እቁበተኞች ጋር መገናኘት ይችላሉሲሉም አክለዋል።

የዲጂታል ዕቁቡ እንደማንኛውም ዕቁብ ዕጣን መሰረት ያደረገ መሆኑን የተናገሩት ዋና ስራ አስኪያጁ ለሁሉምደንበኞች ዕድልን መሰረት አድርጎ እንደሚደርስ ገልጸዋል።

ለምሳሌ የባለ 105 ቀኑ ዕቁብ 105 ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል። በየሳምንቱም 7 ሰዎች ዕጣ ይወጣላቸዋል።በየትኛው ሳምንት ለማን እንደሚደርስ ግን ማንም ማወቅ አይችልምበማለት አቶ ብስራት አብራርተዋል።

የዲጂታል ዕቁብ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ /የተ/የግ/ ከኢትዮቴሌኮም ጋር ስላለው ግንኙነት ድርጅቱን የጠየቅንሲሆን  የቴሌብር ሱፐር አፕን በመጠቀም የገንዘብ ዝውውር እንደሚያደርጉ አጋሮች ከዲጂታል ዕቁብ ጋርምህጋዊ ግንኙነት አለንየሚል ምላሽ አግኝተናል።

አጋሮች የቴሌብር ሱፐር አፕን በመጠቀም የገንዘብ ዝውውር ወደ ማድረግ ስርዐት ከመግባታቸው በፊትህጋዊነታቸውን እንደሚያጣራ የገልጸው ኢትዮቴሌኮም ዲጂታል ዕቁብም በአፑ ግርጌ የተቀመጠውን ደንብናሁኔታ (Terms & Conditions) ተከትሎ እንደሚሰራ አብራርቷል።

ዕጣ የደርሳቸው ዕቁብተኞችም ክፍያቸው በቴሌብር በኩል እየተፈጸመ እንደሚገኝም አረጋግጧል።

ተጨባጭ ስጋት ያላቸው የቴሌብር ደንበኞችም ኢትዮ ቴሌኮምን ማናገር እንደሚችሉ አስታውቋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::