ዘንድሮ በ16 ደረጃዎች ያሽቆለቆለው የኢትዮጵያ የፕረስ ነፃነት አለም አቀፍ ደረጃ

twitter verification

ሚያዚያ 30፣ 2015 ዓ.ም

የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን “ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፣ የመብቶች ሁሉ አንቀሳቃሽ ነው!” በሚል መሪ ቃል ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ በመላው ዓለም ተከብሮ ውሏል።

በዕለቱም ሐሳብን በነጻነት መግለጽ ከመብቶች ጋር ያለውን ጥብቅና የማይነጣጠል ቁርኝትን የሚያወሱ ጥናቶችና  ውይይቶች የቀረቡ ሲሆን የፕሬስ ነጻነት ያለበትን ደረጃ የሚያሳዩ ሪፖርቶችም ይፋ ተደረገዋል።

ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በዕለቱ ይፋ ባደረገው የሀገራት የፕሬስ ነጻነት ደረጃ ሪፖርት ኢትዮጵያን ከ180 ሀገራት 130ኛ ላይ አስቀምጧታል። ይህም ኢትዮጵያን “መጥፎ” ከሚባሉ 42 ሀገራት ተርታ ያሰለፋት ሲሆን ከአምናው አንጻር የ16 ደረጃዎች ማሽቆልቆል የታየበት ነው።

ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ሲደበዥ፣ ሀሠተኛና የተዛባ መረጃ፣ የጥላቻ ንግግር እንዲሁም የሴራ ትንተና ይንሰራፋል። ይህ ደግሞ በማህበረሰቦች መካከል ያለን መተማመን ይሸረሽራል። ህዝብ በመንግስት ላይ ያለውን እምነት ያሰልላል። መብቶችን ይጣሳሉ። ጥላቻ፣ ጥርጣሬ፣ ግጭት፣ ጦርነት፣ ስደት፣ ረሃብ  የየዕለት ክስተቶች ይሆናል።

እንዲህ ካለው ምስቅልቅል ለመውጣት የመብቶች ሁሉ አንቀሳቃሽ ለሆነውን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ግድ ነው።

ለዚህም የዜጎች ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ሰብዓዊ መብት መሆኑ ታውቆ ካለፍርሃት መብታቸውን የሚያንቀሳቅሱበት አውድ ሊከበር ይገባል። ጋዜጠኞች ከስነልቦናዊና ከአካላዊ ጫና ተላቀው ስራቸውን የሚከውኑበት ሰፊ ምህዳር ሊኖራቸው ይገባል። ነጻ ሚዲያዎች ሊጠናከሩ ይገባል።

ይህ ሲሆን  የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ይቀንሳል። የጥላቻ ንግግር ይኮሰምናል። የሴራ ትንተና አድማጭ አልባ እየሆነ ይሄዳል። መተማመን ይጠነክራል። ሁሉም መብቶችም በአዎንታዊነት ይጎለብታሉ።

መንግስትን ጨምሮ ሁሉም ሰው ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲከበር ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲሰራ መልዕክታችን ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::