የአፍሪካን ስፖርት በበላይነት በመምራት የሚታወቁ ኢትዮጵያውያን

Ethiopians known for leading African sports

ህዳር 10፣ 2016 ዓ.ም

ባሳለፍነው ሳምንት አቶ ኢያሱ ወሰን የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን የፌስቡክ ገፅ እንዲሁም በአንዳንድ ሚድያዎች አሳሳች የሆነ መረጃ ተሰራጭቷል።

የቦክስ ፌዴሬሽኑ በፌስቡክ ገፁ “አቶ ኢያሱ የአፍሪካን ስፖርት በበላይነት በመምራት ከቀድሞ የካፍ ፕሬዚዳንት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ በመቀጠል ሁለተኛ ኢትዮጵያዊ አድርጓቸዋል” በማለት መረጃ ያጋራ ሲሆን ሌሎች እንደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያሉ ሚድያዎችም ይህን አስተጋብተዋል።

ይሁንና የአፍሪካ የስፖርት ዘርፍ (በእግር ኳስ) በበላይነት በመምራት አቶ ይድነቃቸው ፈር ቀዳጅ እንደሆኑ ቢታወቅም ከአቶ ኢያሱ በፊት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማይ የአፍሪካ ባድሜንተን ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ሆነው እ.አ.አ ከ2011 እስከ 2013 አገልግለዋል። ማስረጃ: https://olympics.com/ioc/mrs-dagmawit-girmay-berhane

ስለዚህ አቶ ኢያሱ የአፍሪካን ስፖርት በበላይነት በመምራት ከቀድሞ የካፍ ፕሬዚዳንት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ በመቀጠል ሁለተኛ ኢትዮጵያዊ አድርጓቸዋል የሚለው መረጃ አሳሳች እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::