የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢድ አል አረፋ በአልን በማስመልከት ስጦታና ሽልማት አዘጋጅቷል ተብለው ከተሰራጩ ማጭበርበርያዎች እንጠንቀቅ

Commercial bank of Ethiopia scam alert

ሰኔ 21፣ 2015 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ እየተከበረ የሚገኘውን የኢድ በአል በማስመልከት ስጦታና ሽልማት ማዘጋጀቱን የሚገልጹ ጽሁፎች በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተሰራጩ ይገኛሉ። ፌስቡክና ቴሌግራም ደግሞ ይህ መልዕክት በስፋት እየተጋራባቸዉ የሚገኙ የማህበራዊ ትስስር መንገዶች ናቸዉ።

መልዕክቶቹ የተለያዩ ማስፈንጠሪያዎች /links/ በዉስጣቸዉ የያዙና የማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጠቃሚዎች እንዲጎበኟቸዉ የሚጠይቁ ናቸዉ።

ለምሳሌ ፌስቡክ ላይ የተመለከትነዉ መልዕክት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያዘጋጀዉ የሽልማት መጠን 8 ሺህ ዶላር እንደሆነ እና አንድ ሰዉ ሽልማቱን ለማኘት መልዕክቱን ዋትሳፕ እና ቴሌግራም ላይ ለሌሎች ሰዎች ማጋራት እንዳለበት ያትታል።

አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በተረጋገጠዉ የፌስቡክ ገጹ ባጋራዉ መልዕክት በአየር መንገዱ ስም ሀሰተኛ መልዕክቶችና የማጭበርበሪያ ማስፈንጠሪያዎች /links/ እየተጋሩ እንደሆነ አስታዉቆ ነበር። የማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጥቃሚዎችም ከመሰል መጭበርበሮች እንዲጠነቀቁም አሳስቧል።

ሽልማት እና መሰል አጓጊ ጉዳዮችን በመጥቀስ የሰዎችን ቀልብ በመሳብ የሚደረጉ ማጭበርበሮች በየጊዜዉ የምንመለከተዉ ጉዳይ ሆኗል።

ስለዚህም መሰል መረጃዎችን አምነን ማስፈንጠሪያዎቹን /links/ ከመጫናችን እንዲሁም መልዕክቱን ከማጋራታችን በፊት መልዕክቱን ተረጋግተን መመልከት እና የተጠቀሰዉ ተቋም ትክክለኛ ገጽ መሆኑን ማረጋገጥ ከመጭበርበር ሊታደገን ይችላል።

ስለ ክሊክ አጥማጆችና አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢትዮጵያ ቼክ ያዘጋጀዉን አጭር ቪዲዮ /https://fb.watch/dZc5iSQdzE/ / እንመልከት።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::