የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ የዜጎችንና የሀገርን ሁለንተናዊ ደህንነትና ሰላም በሚያናጋ እና በሚያሳስብ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ሰኔ 16፣ 2015 ዓ.ም

  1. የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ የዜጎችንና የሀገርን ሁለንተናዊ ደህንነትና ሰላም በሚያናጋ እና በሚያሳስብ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በሳምንቱ መጀመሪያ ይፋ ያደረገው ሀገራዊ ሪፖርት ማሳየቱ ተገልጿል። ሪፖርቱ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት በአምስት የማህበራዊ ሚድያ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት (በፌስቡክ፣ በቴሌግራም፣ በዩቱዩብ፣ በትዊተር እና በቲክቶክ) ከታህሳስ 23 /2014 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 23/ 2015 ዓ.ም ያለው ስርጭት ላይ ትኩረቱን እንዳደረገ ተጠቅሷል፡፡ በዚህም የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ኣአሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ሪፖርቱ አመላክቷል። የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት አቅራቢዎችን በተመለከተም ዳሰሳ የተደረገባቸው የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጪዎች ተጠቃሚዎችን ለጥቃት የሚያጋልጡ ይዘቶችን ከአገልግሎት አውታራቸው ላይ ለማስወገድ እና ዜጎችን ከጥቃት ለመከላከል በሚያስቀምጡት የማህበረሰብ ጥበቃ ህግና ደንብ መሰረት ተገቢ እርምጃዎችን አለመወሰዳቸውም በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡
  2.  የአክሲዮን ማህበራት በሁሉም መገናኛ ብዙሃን የሚያስተላልፉቸው ማስታወቂያዎች የህግ አግባብን የተከተሉ መሆን እንደሚገባቸው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሳምንቱ አጋማሽ ገልጿል። ሚኒስቴር መስራ ቤቱ ይህን የገለጸው ከካፒታል ገበያ ባለስልጣን ጋር በመተባበር የአክሲዮን ማህበራት በመገናኛ ብዙሃን የሚያስተላልፉቸውን ማስታወቅያዎች አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። የአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቂያዎች በሚዲያ እንዲሁም በተለያዮ አማራጮች ለህብረተሠቡ ተደራሽ ሲደረጉ ህብረተሰቡን ለአላስፈላጊ ኪሳራ እዳያጋልጡ የህግ አግባብን ተከትለው ሊሰሩ እንደሚገባና ህብረተሠቡም ትክክለኛነታቸውን በቅድሚያ ማረጋጋጥ እንደሚኖርበት በመግለጫው ተነስቷል።
  3.  የአውስትራሊያ መንግስት ትዊተር የጥላቻ መልዕክቶችን ስርጭት ለመቆጣጠርና ለመከላከል እያደረገ ያለውን እርምጃ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጠው ዕረቡ ዕለት ጠይቋል። የአውስትራሊያ መንግስት ለትዊተር የ ቀናት የጊዜ ገደብ የሰጠ ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ማብራሪያ የማያገኝ ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚጥል ኣአስታውቋል። ቅጣቱም በቀን 700,000 የአውስትራሊያ እንደሚሆን አስታውቋል።️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

    – በሰኞ መልዕክታችን መረጃን ማጣራትና ተግዳሮቶቹን የተመለከተ ጽሁፍ አስነብበናል:
    https://t.me/ethiopiacheck/2039

    -እንዲሁም ኢትዮ ቴሌኮም የጥሪ ማዕከሉን ዘግቷል በሚል የተሰራጨ መረጃን ፈትሸናል:

    https://t.me/ethiopiacheck/2040

    -የእስራኤል ኢምባሲ ለመግባት ተጨማሪ ቀጠሮ ያዙ የተባሉ ሰዎችን ጉዳይም ተመልክተናል:

    https://t.me/ethiopiacheck/2042

    -የድምጻዊ ሚዛን ተስፋይ የዩቱብ አካውንትን የተመለከተ ማጣራት አድርገናል:
    https://t.me/ethiopiacheck/2043

    -በተመሳሳይ በድምጻዊ ጉቱ አበራ ስም የተከፈቱ የፌስቡክ አካውንቶችን አጣርተናል:
    https://t.me/ethiopiacheck/2044

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::