የአለማችን መጪው ትልቁ ፈተና: የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት

የአለማችን መጪው ትልቁ ፈተና: የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት

ጥር 10፣ 2016

የአለም ኢኮኖሚክ ፎረም (WEF) ከቀናት በፊት የዘንድሮውን የስጋት ሪፖርት (Risk Report) ይፋ አድርጎ ነበር። ሪፖርቱ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት የፈጠረው ስጋትን በሚቀጥሉት ሁለት አመታት ካሉ ስጋቶች በበለጠ በአንደኝነት አስቀምጧል።

“የአለማችንን ሰላም ሊያውኩ የሚችሉ አዳዲስ ስጋቶች እየተከሰቱ ናቸው” የሚለው ሪፖርቱ በሚቀጥሉት ሁለት አመታት ውስጥ ከግጭቶች እና የአየር ለውጥ በላይ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ለአለማችን አሳሳቢ ነው ብሏል።

ሪፖርቱ አክሎም እነዚህ ስጋቶች ለዴሞክራሲያዊ ስርዐቶች ፈተና እየሆኑ እንደመጡ በመጥቀስ ሶስት ቢልዮን ሰዎች በምርጫዎች በቅርብ ግዜያት እንደሚሳተፉ ይገልፃል።

“ታዲያ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት እነዚህን ምርጫዎች የማሰናከል እድል አለው። በተጨማሪም ህዝባዊ አመፆችን፣ ግብግቦችን እና በመንግስት እና ሚድያ ምንጮች ላይ አለመተማመን ሊፈጥር ይችላል። ከሁሉም በላይ ፅንፍ የረገጡ አስተሳሰቦችን እድሉ ሰፊ ነው” በማለት ሪፖርቱ ያስረዳል።

እንደሚታወቀው በሀገራችንም የሀሰት መረጃዎች በበርካታ አካላት በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል። ሶሻል ሚድያ የፈለጉትን የሚሳደቡበት፣ በሀሰት የሚወነጅሉበት፣ ስም የሚያጠፉበት እንዲሁም ስውን ለጥቃት የሚያነሳሱበት ሲሆን ይታያል።

ሶሻል ሚድያ ላይ ሚወጡ የሀሰት መረጃዎች ከበድ ያሉ ችግሮች እንዲፈጠሩ እያደረገ ነው። ለዚህም ሁላችንም ለሀሰት መረጃ ጆሮ አለመስጠት እና ሲገኝም ማጋለጥ ይኖርብናል።

የኢትዮጵያ ቼክ ስራዎችን ለማግኘት እነዚህን ሊንኮች ይከተሉ:

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/EthiopiaCheck/

ትዊተር: https://twitter.com/EthiopiaCheck?s=09

ቴሌግራም: https://t.me/ethiopiacheck

ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/channel/UCKtY61Jdq0jTaJaEe0kik8w

ድረ-ገፅ: ethiopiacheck.org

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::