በምስሉ ላይ የሚታየው የሪክ ማቻር የኢትዮጵያ ፓስፖርት ትክክለኛ ነው

በምስሉ ላይ የሚታየው የሪክ ማቻር የኢትዮጵያ ፓስፖርት ትክክለኛ ነው

ሐምሌ 23፣ 2015

የቀድሞው የደቡብ ሱዳን የተቃዋሚ መሪ፣ አሁን ላይ ደግሞ የሀገሪቱ ምክትል በፕሬዝደንት በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ሪክ ማቻር የኢትዮጵያ ፓስፖርት እንዳላቸው የሚልፁ መረጃዎች ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲዘዋወሩ ተመልክተናል፣ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮችም መረጃውን እንድናጣራ ጥያቄ አቅርበውልናል።

በዚህ ዙርያ በመጀመርያ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የቀድሞው የሪክ ማቻር ቃል አቀባይ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ሉል ሩአይ ሲሆኑ ፓስፖርቱ እ.አ.አ በ 2018 ለሪክ ማቻር ተሰጥቶ እንደነበር አረጋግጠው ይህም “የደቡብ ሱዳን የሰላም ውይይት እንዲፀና ለማስቻል እና ሪክ ማቻር ተንቀሳቅሰው ስብሰባዎችን እንዲካፈሉ በማሰብ በኢትዮጵያ መንግስት የተሰጠ ነው” በማለት አረጋግጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው የሚድያ ዳሰሳ ይህንኑ ማረጋገጥ የቻለ ሲሆን ለምሳሌ “Hot in Juba” የተባለው የደቡብ ሱዳን ኦንላይን ሚድያ ፓስፓርቱ ለሪክ ማቻር በወቅቱ የተሰጠው በዚሁ አመት ግንቦት ወር ላይ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ጋር በአዲስ አበባ ሁለቱ ተቀናቃኞች ባደረጉት የፊት ለፊት ውይይት ውይይት ወቅት እንደሆነ ጠቅሷል።

በዚህም መሰረት ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝደንት ሪክ ማቻር የኢትዮጵያ ፓስፖርት ትክክለኛ እንደሆነ ተረጋግጧል።

ሪክ ማቻር እና ፕሬዝደንት ኪር በሁለት ጎራ ሆነው እ.አ.አ ከ2013 ጀምሮ ባደረጉት የደቡብ ሱዳን ደም አፋሳሽ ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ኋላ ላይ በተደረገ የሰላም ድርድር በሀገሪቱ ሰላም ሰፍኗል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::