የተቀናጀ ተጽኖ የመፍጠር እንቅስቃሴ (Coordinated Infuence Operation) ምንድን ነው?

የተቀናጀ ተጽኖ የመፍጠር እንቅስቃሴ (Coordinated Infuence Operation) ምንድን ነው?

ጥቅምት 7፣ 2016

በማህበራዊ ሚዲያ የሚሳለጡ የመረጃ ልውውጦችን፣ የሀሳብ ግብይቶችን እንዲሁም የንግድ ክንውኖችንየሚያውኩ በርካታ ተዋንያኖች መኖራቸውን በየዕለቱ የምንታዘበው ነው።

አንዳንዶቹ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ሆን ብለው የሚያሰራጩ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ የጥላቻ መልዕክቶችንሲያጋሩ ይስተዋላል። በማጭበርበር ድርጊት የተሰማሩም በርካታ ናቸው።

በሌላ በኩል አጀንዳቸው የብዙሃኑ እንዲሁም ቅቡልነታቸው ሰፊ መሆኑን ለማሳየት ተደራጅተውና ተቀናጅተውጤናማ የመረጃ ፍሰትን የሚያደፈርሱ አካላትም አሉ።

እንዲህ ያሉ አካላት በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሳይቱን አሉታዊ ጸባይ ሜታ ከሁለት አመት በፊት የተቀናጀ ሀሠተኛእንቅስቃሴ (coordinated inauthentic behaviour) በማለት የሰየመው ሲሆን ድርጊቱም ያልተገባ መሆኑንአስምሮበታል። የመስኩ አጥኝዎች በበኩላቸው የተቀናጀ ተጽኖ የመፍጠር እንቅስቃሴ (coordinated infuence operation) ሲሉ ይጠሩታል።

የተቀናጀ ተጽኖ የመፍጠር እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት ግባቸው የሚያራምዱት አጀንዳ የብዙሃኑ፣ቅቡልነታቸው ወይም የድጋፍ መሰረታቸው ሰፊ መሆኑን ማሳየት ነው። ለዚህም በተቀናጀ መልክ በርካታየማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች ይከፍታሉ።

አካውንቶችን ለሚያንቀሳቅሱ ሰዎች ስልጠና ይሰጣሉ። አቅም ያላቸው ደግሞ ሀሰተኛ አካውንቶችንና ቦቶችንየሚፈበርኩ ሶፍትዌሮችን ይጠቀማሉ።

እነዚህ አካውንቶችና ቦቶች የእነሱ ወገን የሆኑ መሪዎች፣ ተቋማት፣ ሚዲያዎች ወይም አክቲቪስቶችበሚያጋሯቸው ይዘቶች ስር ግር ብለው በመምጣት የአስተያየት መስጫ ቦታዎችን በድጋፍ ጽሁፎች ያጨናንቃሉ።እንዲሁም በተቀናጀ መልክ ይዘቶችን በብዛት በማጋራት የሀሳብ ልውውጦችን ይበርዛሉ።

በአንጻሩ ከነሱ በተቃራኒ ወደአሉ አካላት በመሄድ በዘመቻ መልኩ ያሳንሳሉ አልያም ይፈርጃሉ።

በዚህም ሀሰተኛ ቅቡልነትን ለማስረጽ ይሞክራሉ። ዜጎች በያዙት አቋምና አስተያየት ጥርጣሬ እንዲያድርባቸውያደርጋሉ። ጤናማ የሀሳብ ልውውጥን በማወክ የዴሞክራሲ ልምምድን ያቀጭጫሉ። መደናገርም ይፈጥራሉ።

እንዲህ ያሉ አሉታዊ ድርጊቶች ማወቅና ተዋንያኖችንም መለየት በትክክለኛ መረጃ የተመሰረተ አቋምና ሀሳብለመያዝ ያግዘናል።

በተቀናጀ ተጽኖ የመፍጠር እንቅስቃሴ የተሰማሩ አካላትንም በቀላሉ መለየት ይቻላል።

በመጀመሪያ በተቀናጀ ተጽኖ የመፍጠር እንቅስቃሴ የተሰማሩ አካውንቶች ቀድሞ የተዘጋጁና ተመሳሳይነትያላቸውን ይዘቶች (copy paste contents) በማጋራት የሚታወቁ ሲሆን በተጋነነ መልኩ የሚያሞካሹ ቃላትንይጠቀማሉ። እንዲሁም ድጋፍንና ፍቅርን የሚያንጸባርቁ ኢሞጆችን (emojis) ያጋራሉ። አከነሱ በተቃራኒ ለሆኑወገኖች ደግሞ የሚያጣጥሉና የሚፈርጁ ቃላትና ኢሞጆችን ሲጠቀሙ ይታያል።

እንዲሁም በተቀናጀ ተጽኖ የመፍጠር እንቅስቃሴ የተሰማሩ አካውንቶች የተከፈቱበትን ቀን እና የሚጠቀሙትንየፕሮፋይል ምስል መመልከት ማንነታቸውን ለማወቅ ፍንጭ ይሰጣል። እንዲህ ያሉ አካውንቶች በቅርብ ቀንየመከፈት እድላቸው ሰፊ ሲሆን የፕሮፋይል ምስላቸው በአብዛኛው የመሪዎች ወይም የተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣አርማዎች ወይም ሌላ ማንነታቸውን የማያሳይ ፎቶ ሊሆን ይችላል።

በተጨማሪም በተቀናጀ ተጽኖ የመፍጠር እንቅስቃሴ የተሰማሩ አካውንቶች በአስተያየት መስጫ ቦታዎችይዘቶች በተጋሩበት ቅጽበት ግር ብለው መምጣት መለያ ጸባያቸው ነው።

የተቀናጀ ተጽኖ የመፍጠር እንቅስቃሴ ምንነትን በመረዳትና እንቅስቃሴያቸውን በመለየት እራሳችንን ከአሉታዊ ተጽኖ እንጠብቅ!

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::