የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከደንበኞች ሂሳብ ላይ ስለሚደረግ ስርቆት ያጋራው መረጃ

ሰኔ 07፣ 2015 ዓ.ም

ባንኩ ዛሬ ባጋራው መረጃ ባንኩን በማስመሰል ስልክ በመደወል እና ቲክቶክን ጨምሮ የተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ተጠቅመው ከደንበኞች ሂሳብ ላይ ስርቆት የሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች ከሚጠቀሟቸው አሳሳች መልእክቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል ብሏል:

• ባንኩ በሞባይል ባንኪንግ የብድር አገልግሎት መስጠት ስለጀመረ የሚከተለውን ኮድ በማስገባት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ፣

• የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ልናስተካክልዎት ነውና የምንነግርዎትን ቁጥር ወይም ኮድ ያስገቡ፣

• መረጃችሁን በትክክል ስላልሞላችሁ እናስተካክልላችሁ፣

• ሽልማት ስለደረሶት ሽልማቱ እንዲላክልዎት ገንዘብ ያስገቡ፣

• የሞባይል ባንኪንግ ሲስተም አፕዴት ልናደርግልዎት ነው፣

• የሞባይል ባንኪንግ ከፍተንልዎታል፣

• ባንካችን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ይሸልማል፣

• ሌሎችም ተመሳሳይ መልእክቶች።

በመሆኑም ተመሳሳይ መልእክቶች ሲደርሳችሁ ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ አሊያም ወደ 951 በመደወል ትክክለኛነቱን ሳታረጋግጡ ምንም አይነት እርምጃ እንዳትወስዱ እናሳስባለን ብሎ ባንኩ ማሳሰቢያውን አስተላልፏል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::