በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስም ከሚፈፀሙ የማጭበርበር ድርጊቶች ራሳችንን እንጠብቅ

Commercial Bank of Ethiopia

ሐምሌ 28፣ 2015 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስም የሚፈፀሙ በርካታ የማጭበርበር ድርጊቶች እንዳሉ ከዚህ በፊት የተለያዩ መረጃዎችን አቅርበን ነበር።

ከነዚህም መሀል ባንኩ ሽልማት የሚያስገኝ የጥያቄና መልስ መርሃ ግብር እንዳዘጋጀ፣ በሞባይል ባንኪንግ የብድር አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ፣ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ልናስተካክልዎት ነውና የምንነግርዎትን ቁጥር ወይም ኮድ ያስገቡ፣ የባንክ አካውንት መረጃችሁን በትክክል ስላልሞላችሁ እናስተካክልላችሁ፣ ሽልማት ስለደረሶት ሽልማቱ እንዲላክልዎት ገንዘብ ያስገቡ እና ሌሎችም ተመሳሳይ መልእክቶችን በመጠቀም የማጭበርበር ድርጊቶች እንደሚፈፀሙ ይታወቃል።

አሁን ደግሞ ምስሉ ላይ በሚታየው መልኩ ባንኩ በተረጋገጠው የፌስቡክ አካውንቱ ለተገልጋዮች ገንዘብ አካውንታቸው ላይ እንደገባ የሚገልፅ መልዕክት እንደላከ በማስመሰል በቅንብር በመስራት የማጭበርበር ስራዎች እንደሚሰሩ ተመልክተናል።

ባንኩ ከዚህ በፊት ተደጋግሞ እንደገለፀው ትክክለኛ አካውንቶቹ እነዚህ ናቸው፣ ከዚህ ውጭ ያሉትን አምኖ ባለመቀበል ራሳችንን ከመጭበርበር እንጠብቅ:

ድረ-ገፅ: https://www.combanketh.et

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/combanketh

ትዊተር: https://twitter.com/combankethiopia

ቴሌግራም https://t.me/combankethofficial

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::