“በአሁኑ ወቅት በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የብድር አገልግሎት በመስጠት ላይ አይደለንም” – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Commercial bank of Ethiopia scam alert

ግንቦት 21፣ 2015 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት አማካኝነት የብድር አገልግሎት እየሰጠ ነው በሚል የሀሰት መረጃ ስርቆት ለመፈፀም የሚሞክሩ አጭበርባሪ መልእክቶች እየተሰራጩ እንደሚገኙ ዛሬ አስታውቋል።

ባንኩ እንዳለው እነዚህ የማጭበርበርያ መልዕክቶች ደንበኞች ብድር ለማግኘት እንዲጠቀሙበት ባስቀመጡት ሀሰተኛ ኮዶች አማካኝነት ከደንበኞች ሂሳብ ላይ ገንዘብ ለመስረቅ እየሞከሩ ነው፡፡

“ነገር ግን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ወቅት በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የብድር አገልግሎት በመስጠት ላይ አይደለም። በመሆኑም ደንበኞች ከንደዚህ ዓይነት አጭበርባሪዎች እራሳችሁን እየጠበቃችሁ ባንኩ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች መረጃ ማግኘት ያለባችሁም ከግለሰቦች ሳይሆን ከባንኩ ቅርንጫፎች፣ ወደ 951 በመደወል እና ከባንኩ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ መሆን እንዳለበት እንገልጻለን” ብሏል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::