በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የሕጻናት እርቃን ምስሎች በስፔን ድንጋጤ ፈጠሩ

TikTok agrees to have its content moderated in Kenya

መስከረም 18፣ 2016

  1. የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጠው ኤክስ ፖለቲካን የተመለከቱ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች ሪፖርት የሚደረጉበትን አገልግሎት ማቋረጡን ሮይተርስ ዘግቧል። አገልግሎቱ በተለይም ምርጫን የተመለከቱ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ለመከታተልና ለመቆጣጠር ታስቦ እአአ በ2022 ነበር ወደስራ የገባው። ኩባንያው አገልግሎቱን ለምን እንዳቋረጠ አለመግለጹ በዘገባው ተካቷል።
  1. የህንድ ማዕከላዊ መንግስት የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን የሚገዛ ረቂቅ ህግ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን ሂንዱስታን ታይምስ ዘግቧል። ዲጅታል ኢንዲያ ቢል የሚል ስያሜ ያለው አዲሱ ህግ ከቴክኖሎጅ እድገት ጋር በተገናኘ በመከሰት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ለማካተት ያለመ መሆኑንና ከ23 ዓመት በፊት የወጣው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ህግ እንደሚተካ በዘገባው ተጠቅሷል። ህጉ ከሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች በተጨማሪ ኢንተርኔትን መሰረት ያደረጉ የማጭበርበር ድርጊቶችን ይገዛል ተብሏል።
  1. በደቡባዊ ስፔን የምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተማ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች እርቃን ምስሎች ከእነርሱ እውቅና ውጭ በማኅበራዊ ሚዲያ ከተዘዋወሩ በኋላ ድንጋጤ መፈጠሩን ቢቢሲ ዘግቧል። እርቃን ምስሎቹ የተሰሩት ሙሉ ልብስ ለብሰው የተነሱትን የታዳጊዎቹን ፎቶ በመጠቀም ሲሆን በርካታ ምስሎቹ የተወሰዱትም ከታዳጊዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች መሆኑ በዘገባው ተካቷል። እስካሁን ዕድሜያቸው በ11 እና በ17 ዓመት መካከል የሚገኙ 20 ታዳጊ ሴቶች፣ የዚህ ድርጊት ሰለባ መሆናቸውን የተገልውጸ ሲሆን ፖሊስ ድርጊቱን እየመረመረ ነው ተብሏል።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው፥

– በሰኞ መልዕክታችን ማህበራዊ ሚዲያዎች ከሰላም ግንባታ አኳያ የሚኖራቸውን ሚና የቃኘ ጽሁፍ አስነብበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2196

– እንዲሁም በጎንደር የተከሰተን የእሳት ቃጠሎ ያሳያል የተባለ ቪዲዮን ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2197

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::