በአፍሪካ ልማት ባንክ ሁለት ሰራተኞች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ድብደባ መፈፀሙ ትክክለኛ መረጃ መሆኑ ድርጅቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል

African Development Bank employees beaten in Ethiopia

ህዳር 6፣ 2016 ዓ.ም

በርካታ የዲጂታል ሚድያዎች ከቀናት በፊት በአፍሪካ ልማት ባንክ የስራ ሀላፊዎች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ድብደባ መፈፀሙን ሲዘግቡ ነበር።

እነዚህ ዘገባዎች ድብደባ ከደረሰባቸው ግለሰቦች መሀል የባንኩ የኢትዮጵያ ማናጀር የሆኑት አብዱል ካማራ እንደሚገኙበት ገልፀው ነበር።

ባንኩ ዛሬ በድረ-ገፁ ይፋ እንዳደረገው ጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ/ም ሁለት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የባንኩ ባልደረባዎች በፀጥታ አካላት “ህገወጥ” በሆነ መልኩ ለበርካታ ሰአታት መታሰራቸውን እና አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው አስታውቋል።

ባንኩ በመግለጫው ባይጠቅሰውም ኢትዮጵያ ቼክ ከአንድ የባንኩ ሀላፊ ባገኘው መረጃ ድብደባ የደረሰባቸው አንደኛው ግለሰብ ዲጂታል ሚድያዎች ላይ እንደተዘገበው የባንኩ የኢትዮጵያ ማናጀር የሆኑት አብዱል ካማራ ናቸው።

“የኢትዮጵያው ጠ/ሚር ድርጊቱ እንደተፈፀመ እንደሰሙ ወዲያውኑ ግለሰቦቹ ከእስር እንዲለቀቁ እና ምርመራ እንዲደረግ አድርገዋል” ያለው ባንኩ ድርጊቱን ግን “በጣም ከፍተኛ የዲፕሎማቲክ አድራጎት” ብሎታል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::