አመታዊው የአፍሪካ ፋክትስ ሰሚት (Africa Facts Summit) በሞሪሽየስ መካሄድ ጀመረ

አመታዊው የአፍሪካ ፋክትስ ሰሚት (Africa Facts Summit) በሞሪሽየስ መካሄድ ጀመረ

መስከረም 24፣ 2016

በአፍሪካ የሚገኙ መረጃ አጣሪ ተቋማትና ኤክስፐርቶችን የሚያሳትፈው አመታዊው የአፍሪካ ፋክትስ ሰሚት (ጉባዔ) በሞሪሽየስ መካሄድ ጀምሯል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየውና ኢትዮጵያ ቼክን ጨምሮ ከ200 በላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ መረጃ አጣሪ ተቋማት ተወካዮችና ኤክስፐርቶች የሚሳተፉበት የ2023 ዓም ጉባዔ በአፍሪካ ቼክ እና ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሞሪሺየስ ትብብር የተዘጋጀ ነው።

ጉባዔው መረጃ አጣሪ ተቋማትና ኤክስፐርቶች የሐሰተኛና አሳሳች መረጃዎችን ስርጭት ለመግታት ልምድና ሀሳብ የሚለዋወጡበት መድረክ ነው።

የዚህ ዓመት ጉባዔም ‘ገለልተኛ መረጃ አጣሪነትን በአህጉሪቱ መገንባት’ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።

በተጨማሪ በጉባዔው የሐሰተኛ መረጃዎችን ስርጭትን ለመግታት የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ሚና፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ከሐሰተኛ መረጃ ስርጭት አንጻር የደቀነው ፈተና እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመዋጋት ያለው ሚና እንዲሁም የጥላቻ ንግግርን የተመለከቱ ውይይቶች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::