በአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዙርያ የቀረቡ ጥያቄዎች እና የተሰጡ ምላሾች

Admas Digital lottery

ሐምሌ 27፣ 2015 ዓ.ም

በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮች የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ እጣ የሚወጣባቸውን ቀኖች በተመለከተ ማብራሪያ እንድንጠይቅላቸው መልዕክቶች ልከውልናል።

መልዕክቶችን የላኩልን ተከታታዮች የአድማስ ዲጂታል ሎተሪን ከቆረጡ በኃላ እጣው የሚወጣበት ቀን በግልጽ ስለማይነገር ጥርጣሬ እንዳሳደረባቸው ገልጸውልናል።

ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን በተመለከተ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርን ማብራሪያ ጠይቋል።

የአስተዳደሩ የኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ ቴውድሮስ ነዋይ “ይህ አይነቱ ጥያቄ በተደጋጋሚ ወደኛም ይመጣ ነበር። ሆኖም ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ እጣ የሚወጣባቸውን ቀኖች በግልጽ ማሳወቅ ጀምረናል” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

በዚህም ዲጅታል ሎተሪውን ለቆረጡ ደምበኞች ክፍያቸውን ከፈጸሙ በኋላ በ605 የአጭር መልዕከት ቁጥር በኩል የእጣው ቁጥር፣ እጣው የሚያበቃበት ቀን እና እጣው የሚወጣበት ቀን እንደሚላክ ነግረውናል።

አሁን በመካሄድ ላይ ያለው የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ እጣው የሚያበቃበት ቀን ነሐሴ 25/2015 ዓ.ም ከለሊቱ 6 ሰዐት መሆኑንና  እጣው የሚወጣበት ቀን ነሐሴ 29/2015 ዓ.ም  መሆኑንም ጨምረው ነግረውናል።

የኢትዮጵያ ቼክ ባልደረባም የአድማስ ዲጅታል ሎተሪን በመቁረጥ ከላይ የተገለጹት መረጃዎች በ605 የአጭር መልዕከት ቁጥር እንደሚላኩ አረጋግጧል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::