“ሀሰተኛ ዜና ነው። እኔ ስራዬ ላይ ነው ያለሁት”— የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮሀንስ አያሌው

"ሀሰተኛ ዜና ነው። እኔ ስራዬ ላይ ነው ያለሁት"--- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮሀንስ አያሌው

ጥቅምት 14፣ 2016

ኦሮሚያ ሚድያ ኔትዎርክ (OMN) ከሰሞኑ በሰራቸው ዘገባዎቹ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት / ዮሀንስአያሌው ከስራቸው ተነስተው በምትካቸውም ሌላ ሰው ስለመሾሙ መስማቱን ዘግቧል።

በዘገባውም ባንኩ በአንድ ብሄር ተወላጆች ስለመያዙ እና አግላይና ሌሎች ብልሹ አሰራሮች በድርጅቱ ውስጥመስፈናቸውን ይጠቅሳል።

ይሁንና የባንኩ ሁለት ሰራተኞች መረጃው የተሳሳተ እንደሆነ እና የስራ ገበታቸው ላይ እንደሚገኙ ለኢትዮጵያ ቼክበሰጡት ጥቆማ መሰረት ለዶ/ ዮሀንስ በዚህ ዙርያ ጥያቄ ያቀረብን ሲሆንሀሰተኛ ዜና ነው። እኔ ስራዬ ላይነው ያለሁትብለው ምላሽ ሰጥተዋል።

ባንኩ ከአራት ቀን በፊት ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በይፋ ባሳወቀበት ፕሮግራም ላይም/ ዮሀንስ ተገኝተው እንደነበር የኢትዮጵያ ልማት ልማት ባንክ የፌስቡክ ገፅ ላይ ከተለጠፉ ፎቶዎችተመልክተናል።

ስለዚህ የባንኩ ፕሬዝደንት እንደተነሱ ተደርጎ OMN የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::